Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:60 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

60 ኢየሱስም “ሙታንን ተዋቸው፤ ሙታኖቻቸውን ይቅበሩ፤ አንተ ግን ሂድና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት አስተምር!” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

60 ኢየሱስም፣ “ሙታን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው፤ አንተ ግን ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

60 ኢየሱስም፦ “ሙታኖቻቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት አስተምር፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

60 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ሙታ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን ይቀ​ብሩ ዘንድ ሙታ​ንን ተዉ​አ​ቸው፤ አንተ ግን ሂድና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት ስበክ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

60 ኢየሱስም፦ ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት ስበክ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:60
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም በምኲራቦቻቸው እያስተማረና የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ፥ በልዩ ልዩ በሽታና ደዌ የተያዙትንም ሰዎች እየፈወሰ በገሊላ ምድር ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ኢየሱስም “አንተ እኔን ተከተለኝ፤ ሙታንን ግን ሙታናቸውን እንዲቀብሩ ተዋቸው” አለው።


ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፥ እነሆ፥ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶ ነበር፤ ተገኘ’፤ መደሰትም ጀመሩ።


ይህ ወንድምህ ግን ሞቶ ነበር፤ አሁን በሕይወት አለ፤ ጠፍቶ ነበር፤ አሁን ተገኘ፤ ስለዚህ በጣም ልንደሰት ይገባናል።’ ”


ወንጌልን ማስተማር ግዴታዬ ስለ ሆነ የምመካበት ነገር አይደለም፤ እንዲያውም ወንጌልን ሳላስተምር ብቀር ወዮልኝ!


እናንተ በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ምክንያት በመንፈሳዊ ኑሮአችሁ የሞታችሁ ነበራችሁ፤


በበደላችን የሞትን ብንሆንም እንኳ እግዚአብሔር ከክርስቶስ ጋር እንድንኖር አድርጎናል፤ እናንተም የዳናችሁት በጸጋው ነው።


የዚህን ዓለም ደስታ ብቻ የምትወድ መበለት ግን በቁሟ የሞተች ናት።


ቃሉን ስበክ፤ ቢመችም ባይመችም በማንኛውም ጊዜ ተግተህ ሥራ፤ እያስረዳህ እየገሠጽክና እየመከርክ፥ በትዕግሥትና በማስተማር ትጋ።


አንተ ግን በሁሉ ነገር ጥንቁቅ ሁን፤ መከራን በመቀበል ጽና፤ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አከናውን፤ አገልግሎትህንም ሁሉ ፈጽም።


“ለሰርዴስ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፤ “ይህ፥ ሰባቱን የእግዚአብሔር መንፈሶችና ሰባቱን ኮከቦች ከያዘው የተነገረ ነው፤ ሥራህን ዐውቃለሁ፤ በስም ሕያው ነህ፤ ነገር ግን ሞተሃል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች