Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:58 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

58 ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ የሰማይ ወፎችም ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ አስጠግቶ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም፤” ሲል መለሰለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

58 ኢየሱስም፣ “ቀበሮዎች ጕድጓድ፣ የሰማይ ወፎችም ጐጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ዐንገቱን እንኳ የሚያስገባበት የለውም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

58 ኢየሱስም፦ “ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች ጎጆ አላቸው፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ምንም ስፍራ የለውም፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

58 ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም “ለቀ​በ​ሮ​ዎች ጕድ​ጓድ አላ​ቸው፤ ለሰ​ማይ ወፎ​ችም ጎጆ አላ​ቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን የሚ​ያ​ስ​ጠ​ጋ​በት የለ​ውም” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

58 ኢየሱስም፦ ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:58
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሤና አምላኬ የሠራዊት ጌታ ሆይ! ድንቢጦች ለመኖሪያቸው ጎጆ ሠርተዋል፤ ዋኖሶችም ጫጩቶቻቸውን የሚያኖሩበት በመሠዊያዎችህ አጠገብ ቤት አላቸው።


እርስዋ ከዘር ሁሉ ያነሰች ናት ባደገች ጊዜ ግን፥ ከአትክልቶች ሁሉ ትበልጣለች፤ ዛፍም ትሆናለች፤ ወፎችም መጥተው በቅርንጫፎችዋ ላይ ጎጆአቸውን ሠርተው ይሰፍሩባታል።”


ኢየሱስም “ቀበሮዎች ጒድጓድ አላቸው፤ በአየር ላይ የሚበሩ ወፎችም የሚሰፍሩበት ጎጆ አላቸው፤ የሰው ልጅ ግን ራሱን እንኳ የሚያሳርፍበት ስፍራ የለውም” ሲል መለሰለት።


እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።


የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች