Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

40 ርኩሱን መንፈስ እንዲያስወጡለት ደቀ መዛሙርትህን ጠይቄአቸው ነበር፤ ነገር ግን አልቻሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

40 ደቀ መዛሙርትህ እንዲያወጡለት ለመንኋቸው፤ ነገር ግን አልቻሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

40 ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፤ እነርሱ ግን አልቻሉም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

40 እን​ዲ​ያ​ወ​ጡ​ትም ደቀ መዛ​ሙ​ር​ት​ህን ለመ​ን​ሁ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ማው​ጣት ተሳ​ና​ቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

40 ደቀ መዛሙርትህንም እንዲያወጡት ለመንሁ፥ አልቻሉምም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:40
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ግያዝም ወደ ፊት ቀድሞአቸው ሄደና የኤልሳዕን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኖረ፤ ነገር ግን ድምፅም ሆነ ሌላ የሕይወት ምልክት አልነበረም፤ ስለዚህም ተመልሶ ሄዶ ኤልሳዕን “ልጁ አልተነሣም” አለው።


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “እምነታችሁ ጐደሎ ስለ ሆነ ነው፤ በእውነት እላችኋለሁ፤ የሰናፍጭ ቅንጣት የሚያኽል እምነት ቢኖራችሁ ይህን ተራራ ‘ከዚህ ተነሥተህ ወዲያ ሂድ!’ ብትሉት ይሄዳል፤ የሚሳናችሁም ምንም ነገር አይኖርም።


ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ሐዋርያት ወደ እርሱ ጠርቶ አጋንንትን የማውጣትና ደዌንም ሁሉ የመፈወስ ኀይልና ሥልጣን ሰጣቸው።


እነሆ! ርኩስ መንፈስ በድንገት ይዞ ያስጮኸዋል፤ በመሬት ላይ ጥሎ ዐረፋ እያስደፈቀ ያንፈራግጠዋል፤ ሰውነቱንም እያቈሰለ በአሳር ይለቀዋል።


ኢየሱስም እንዲህ አለ፦ “እናንተ እምነት የሌላችሁ ጠማማ ትውልድ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? እስቲ ልጅህን ወዲህ አምጣው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች