Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 9:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 በዚህ ጊዜ ጴጥሮስና ጓደኞቹ በእንቅልፍ ተሸንፈው ተኝተው ነበር፤ በነቁ ጊዜ ግን የኢየሱስን ክብርና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሁለቱን ሰዎች አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ጴጥሮስና ዐብረውት የነበሩት ግን እንቅልፍ ተጭኗቸው ነበር፤ ሲነቁ ግን ክብሩንና ከርሱ ጋራ የቆሙትን ሁለት ሰዎች አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ተጫጭኖአቸው ነበር፤ ነቅተውም ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ጴጥ​ሮ​ስ​ንና ከእ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ት​ንም ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው በእ​ን​ቅ​ልፍ ፈዝ​ዘው አገኘ፤ በነ​ቁም ጊዜ ክብ​ሩ​ንና ከእ​ርሱ ጋር ቆመው የነ​በ​ሩ​ትን ሁለት ሰዎች አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ነገር ግን ጴጥሮስንና ከእርሱ ጋር የነበሩት እንቅልፍ ከበደባቸው፤ ነቅተው ግን ክብሩንና ከእርሱ ጋር ቆመው የነበሩትን ሁለት ሰዎች አዩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 9:32
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከእንግዲህ ወዲህ ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት አያበሩልሽም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።


የሰውዬውን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ በመደንገጥ ኅሊናዬን ስቼ በመሬት ላይ ወደቅኹ፤ በግንባሬም እንደ ተደፋሁ ቀረሁ።


እርሱም በሚናገርበት ጊዜ ኅሊናዬን ስቼ በግንባሬ ወደ መሬት ተደፋሁ፤ እርሱ ግን ዳሰሰኝና ከመሬት አንሥቶ በእግሮቼ አቆመኝ።


ደግሞም ተመልሶ በመጣ ጊዜ፥ ዐይኖቻቸው በእንቅልፍ ከብደው ስለ ነበር፥ ተኝተው አገኛቸው፤ የሚመልሱለትንም አያውቁም ነበር።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በመካከላችን ኖረ፤ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ እንዳለው ያለውን ክብሩን አይተናል።


“አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር ስለ ወደድከኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ እነዚህ አንተ የሰጠኸኝም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲኖሩ እወዳለሁ።


ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኀይልና ስለ ዳግመኛ መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ በሰው ተንኰል የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፤ ወደፊት ምን እንደምንሆንም ገና አልታወቀም፤ ነገር ግን ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ እውነተኛ መልኩን ስለምናይ እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች