Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 8:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ስለዚህ አጋንንቱ ከሰውየው ወጥተው በዐሣማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ዐሣማዎቹ ከገደሉ ላይ እየተንደረደሩ ወረዱ፤ ወደ ባሕር ገብተውም ሰጠሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 አጋንንቱም ከሰውየው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ የዐሣማውም መንጋ በገደሉ አፋፍ ቍልቍል በመንደርደር ባሕሩ ውስጥ ገብቶ ሰጠመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 አጋንንቱም ከሰውዬው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ሐይቁ ተጣድፎ በመውረድ ሰጠመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እነ​ዚያ አጋ​ን​ን​ትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥ​ተው ወደ እሪ​ያ​ዎች ገቡ፤ የእ​ሪ​ያ​ዎ​ችም መንጋ አብ​ደው ከገ​ደሉ ወደ ባሕር ጠል​ቀው ሞቱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 አጋንንትም ከሰውዬው ወጥተው ወደ እሪያዎች ገቡ፥ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና ሰጠሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 8:33
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስም “ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህም ከሰዎቹ ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ሄዱና ገቡባቸው። ዐሣማዎቹም በሙሉ ከገደሉ አፋፍ ላይ እየተንደረደሩ ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።


አንድ ቀን ኢየሱስ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ሳለ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ቀርበው የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት ይጋፉ ነበር።


በዚያም ስፍራ በኮረብታ ጥግ የብዙ ዐሣማዎች መንጋ ተሰማርቶ ነበር፤ አጋንንቱ “ወደ ዐሣማዎቹ እንድንገባ ፍቀድልን” ሲሉ ኢየሱስን ለመኑት፤ እርሱም ፈቀደላቸው።


የዐሣማዎቹም እረኞች የሆነውን ነገር ባዩ ጊዜ ሸሽተው ሄዱ፤ በየከተማውና በየገጠሩም ወሬውን አዳረሱ።


እናንተ የአባታችሁ የዲያብሎስ ልጆች ናችሁ፤ ፍላጎታችሁም የአባታችሁን ምኞት መፈጸም ነው፤ እርሱ ከመጀመሪያ አንሥቶ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነት በእርሱ ስለሌለ ከእውነት ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፤ እርሱ ሐሰተኛና የሐሰት ሁሉ አባት ስለ ሆነ ሐሰት በሚናገርበት ጊዜ ከገዛ ራሱ አውጥቶ ይናገራል።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ በዙሪያችሁ ይንጐራደዳል።


ንጉሥም ነበራቸው፤ እርሱ የጥልቁ ጒድጓድ መልአክ ነው፤ ስሙም በዕብራይስጥ አባዶን፥ በግሪክ አጶልዮን ይባላል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች