Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 16:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 “አብርሃም ግን ‘ለእነርሱ የሙሴና የነቢያት መጻሕፍት አሉላቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 “አብርሃም ግን፣ ‘ሙሴና ነቢያት አሏቸው፤ እነርሱን ይስሙ’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 አብርሃም ግን ‘ሙሴና ነቢያት አሉላቸው፤ እነርሱን ይስሙ፤’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 አብ​ር​ሃ​ምም፦ ‘ሙሴና ነቢ​ያት አሉ​አ​ቸው፤ እነ​ር​ሱን ይስሙ’ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 አብርሃም ግን፦ ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 16:29
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ ሕያዋን ፍጥረት ሁሉ በእግዚአብሔር መጽሐፍ የተጻፈውን ፈልጋችሁ አንብቡ፤ ከእነዚህ ፍጥረቶች አንዱ እንኳ አይጠፋም፤ የኑሮ ጓደኛ አጥቶ ብቻውን የሚኖርም አይገኝም፤ እግዚአብሔር ራሱ ይህ እንዲሆን ስላዘዘ እርሱ ራሱ በኅብረት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል።


ይህን ቃል ባይናገሩ በእርግጥ የንጋት ብርሃን አይበራላቸውም።


እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።


ኢየሱስ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “የሕግና የነቢያት መጻሕፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ድረስ ሲነገሩ ቈይተው ነበር፤ ከዚያም ወዲህ የሚነገረው የእግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች ቃል ነው፤ እያንዳንዱም ሰው ወደዚያች መንግሥት ለመግባት ብርቱ ጥረት ያደርጋል።


ከዚህ በኋላ ከሙሴና ከነቢያት መጻሕፍት ጀምሮ በቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ ስለ እርሱ የተነገረውን እየጠቀሰ አስረዳቸው።


የነቢዩ ኢሳይያስ መጽሐፍ ተሰጠው፤ መጽሐፉንም በገለጠ ጊዜ፥ እንዲህ ተብሎ የተጻፈበትን ቦታ አገኘ፤


ከጥንቱም ጀምሮ የሙሴ ሕግ በየሰንበቱ በምኲራቦች ይነበብ ነበር፤ ቃሉም በየከተማው ይሰበካል።”


እናንተ ለሕግ ተገዢዎች ሆናችሁ መኖር የምትፈልጉ እስቲ ንገሩኝ፤ ሕግ የሚለውን አትሰሙምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች