Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ዘመድሽ ኤልሳቤጥ እንኳ መኻን ስትባል ኖራ አሁን በስተእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ ከፀነሰችም እነሆ፥ ስድስተኛ ወርዋ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 እነሆ፤ ዘመድሽ ኤልሳቤጥም በስተ እርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን የተባለችውም ስድስተኛ ወሯን ይዛለች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እነሆ ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርሷ ደግሞ በስተርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፤ መካን ትባል ለነበረችው ለእርሷም ይህ ስድስተኛ ወሯ ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እነሆ፥ ከዘ​መ​ዶ​ችሽ ወገን የም​ት​ሆን ኤል​ሣ​ቤ​ጥም እር​ስዋ እንኳ በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ፀን​ሳ​ለች፤ መካን ትባል የነ​በ​ረ​ችው ከፀ​ነ​ሰች እነሆ፥ ይህ ስድ​ስ​ተኛ ወር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እነሆም ዘመድሽ ኤልሳቤጥ፥ እርስዋ ደግሞ በእርጅናዋ ወንድ ልጅ ፀንሳለች፥ ለእርስዋም መካን ትባል ለነበረችው ይህ ስድስተኛ ወር ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:36
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሣራይ መኻን በመሆንዋ ልጅ አልወለደችም ነበር።


የአብራም ሚስት ሣራይ ገና ልጅ አልወለደችለትም ነበር፤ ነገር ግን አጋር የምትባል አንዲት ግብጻዊት አገልጋይ ነበረቻት፤


አብርሃምና ሣራ በዕድሜአቸው መግፋት አርጅተው ነበር፤ የሣራም፥ ልጅ የመውለጃ ዕድሜዋ አልፎ ነበር።


ስለዚህም ፀንሳ በእርጅናው ጊዜ ለአብርሃም ወንድ ልጅ ወለደችለት፤ ልጁም የተወለደው “በዚህ ጊዜ ይወለዳል” ብሎ እግዚአብሔር በተናገረበት ጊዜ ነው።


ነገር ግን ሴቲቱ ፀነሰች፤ ልክ ኤልሳዕ የተናገረው ጊዜ ሲደርስ በተከታዩ ዓመት ወንድ ልጅ ወለደች።


ስለዚህም እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፥ ለመወለድ ጊዜ አለው፤ ለመሞትም ጊዜ አለው፤ ለመትከል ጊዜ አለው፤ ለመንቀል ጊዜ አለው።


መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል፤ የልዑል እግዚአብሔርም ኀይል በአንቺ ላይ ይሆናል፤ ስለዚህ ከአንቺ የሚወለደው ሕፃን ቅዱስ ነው፤ የእግዚአብሔርም ልጅ ይባላል።


ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለም።”


ሄሮድስ በይሁዳ ምድር ንጉሥ በነበረበት ዘመን፥ ከአብያ የክህነት አገልግሎት ክፍል የሆነ ዘካርያስ የሚባል ካህን ነበር። እርሱም ከአሮን ዘር የምትወለድ ኤልሳቤጥ የምትባል ሚስት ነበረችው።


ሣራም ተስፋ የሰጣት እግዚአብሔር ታማኝ መሆኑን ስላወቀች ምንም እንኳ በዕድሜ በመግፋቷ መውለድ የማትችል ብትሆን የመፅነስን ኀይል ያገኘችው በእምነት ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች