Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 21:38 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ከጋድ ግዛት ተከፍለው ከግጦሽ ምድራቸው ጋር የተሰጡአቸው አራት ከተሞች ከመማጸኛ ከተሞች አንድዋ የሆነችው በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ከጋድ ነገድ፣ በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማሪያዋን፥ መሃናይምንና መሰማሪያዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከጋ​ድም ነገድ ለነ​ፍሰ ገዳይ መማ​ፀኛ ከተማ የሆ​ነ​ች​ውን በገ​ለ​ዓድ ውስጥ ራሞ​ት​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፥ ቃሚ​ን​ንና መሰ​ማ​ር​ያ​ዋን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰምርያዋን፥ መሃናይምንና መሰምርያዋን፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 21:38
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ባያቸውም ጊዜ “እግዚአብሔር ከሠራዊቱ ጋር የሚሠፍርበት ቦታ ነው” አለ፤ ስለዚህ ያንን ቦታ ማሕናይም ብሎ ጠራው።


አቤሴሎምና እስራኤላውያን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ በተሻገሩ ጊዜ ዳዊት ማሕናይም ተብላ ወደምትጠራው ትንሽ ከተማ ደርሶ ነበር፤


ባርዚላይ ሰማኒያ ዓመት የሞላው ሽማግሌ ሰው ነበር፤ በጣም ሀብታም ከመሆኑም የተነሣ ንጉሥ ዳዊት በማሕናይም በነበረበት ጊዜ ይኸው ባርዚላይ ምግብ ያቀርብለት ነበር፤


የሳኦል ሠራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር ከሳኦል ልጅ ከኢያቡስቴ ጋር የዮርዳኖስን ወንዝ በመሻገር ወደ ማሕናይም ሸሽቶ ሄደ፤


አክዓብ ባለሟሎቹ የሆኑትን ባለሥልጣኖች “በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትን ከሶርያ ንጉሥ ለማስመለስ ምንም ዐይነት እርምጃ ያልወሰድነው ስለምንድን ነው? ራሞት እኮ የእኛ ይዞታ ናት!” አላቸው፤


በገለዓድ ራሞት ቤን ጌቤር ተብላ የምትጠራው ከተማ፥ በገለዓድ የምናሴ ዘር የሆነው የያኢር ጐሣ ይዞታዎች የሆኑት መንደሮች፥ በባሳን አርጎብ ተብላ የምትጠራው ግዛት፥ እንዲሁም በሮቻቸው የነሐስ መወርወሪያ ባሉአቸው የቅጽር ግንቦች የተመሸጉ በድምሩ የስድሳ ታላላቅ መንደሮች አስተዳዳሪ፤


አሒናዳብ የተባለው የዒዶ ልጅ፦ የማሕናይም ክፍለ ሀገር ገዢ፤


በጋድ ግዛት በገለዓድ የምትገኘው ራሞት፥ ማሕናይም፥


ስለዚህም ለሮቤል ነገድ ከፍታ ባለው በረሓ የምትገኘው የቤጼር ከተማ፥ ለጋድ ነገድ በገለዓድ ግዛት የምትገኘው ራሞትና፥ ለምናሴም ነገድ በባሳን ግዛት ውስጥ የምትገኘው ጎላን እንዲለዩ አደረገ።


የምድራቸውም ስፋት ከሐሴቦን ተነሥቶ እስከ ራማት ምጽጳና እስከ ቤጦኒም እንዲሁም ከማሕናይም ተነሥቶ እስከ ሎዴባር ድንበር ይደርሳል፤


ግዛታቸውም ማሕናይምንና ባሳንን ሁሉ ያጠቃልላል፤ ይህም ባሳን መላውን የባሳን ንጉሥ የዖግን ግዛት እንዲሁም በባሳን በተለይ ያኢር ተብላ በምትጠራው ስፍራ የሚገኙትን ሥልሳ ከተሞች ሁሉ ይጨምራል፤


በምሥራቅ ዮርዳኖስ፥ ከኢያሪኮም በስተ ምሥራቅ ከፍ ብሎ በሚገኘው በረሓማ አገር፥ በሮቤል ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ቤጼርን፥ በጋድ ግዛት ውስጥ በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ግዛት በባሳን የምትገኘውን ጎላንን መርጠው ለዩ፤


ቀዴሞትና ሜፋዓት ናቸው፤


ሐሴቦንና ያዕዜር ናቸው፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች