Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 11:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ይህች ማርያም የጌታን እግር ሽቶ የቀባችውና በጠጒርዋ ያበሰችው ናት፤ የታመመውም አልዓዛር የእርስዋ ወንድም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህች ወንድሟ አልዓዛር የታመመባት ማርያም፣ ጌታን ሽቱ ቀብታ እግሮቹን በጠጕሯ ያበሰችው ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ማርያም ጌታን ሽቱ የቀባችው፥ እግሩንም በጠጉርዋ ያበሰችው ስትሆን፤ የታመመውም አልዓዛር ወንድምዋ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ማር​ያም ግን ጌታ​ች​ንን ሽቱ የቀ​ባ​ችው፥ እግ​ሩ​ንም በጠ​ጕ​ርዋ ያሸ​ችው ናት፤ ወን​ድ​ምዋ አል​ዓ​ዛ​ርም ታሞ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ማርያምም ጌታን ሽቱ የቀባችው እግሩንም በጠጕርዋ ያበሰሰችው ነበረች፤ ወንድምዋም አልዓዛር ታሞ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 11:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኢየሱስ በቢታንያ ለምጻም በነበረው በስምዖን ቤት ነበር። በገበታም ቀርቦ ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ ውድ የሆነና የከበረ የናርዶስ ሽቶ የሞላበት፥ የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ መጣች፤ ብልቃጡን ሰብራ ሽቶውን በኢየሱስ ራስ ላይ አፈሰሰችው።


ጌታም ባያት ጊዜ ራራላትና “አይዞሽ፥ አታልቅሺ!” አላት።


“ያ ይመጣል የተባለው መሲሕ አንተ ነህን ወይስ ሌላ እንጠብቅ? ብላችሁ ጠይቁት፤” ሲል ወደ ጌታ ኢየሱስ ላካቸው።


ማርታ ኢየሱስን፥ “ጌታ ሆይ! አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ፥ ወንድሜ ባልሞተም ነበር፤


እኅትማማቾቹም “ጌታ ሆይ፥ ያ የምትወደው ታሞአል” ብለው ወደ ኢየሱስ ላኩበት።


ማርያም ኢየሱስ ወደ ነበረበት መጥታ ባየችው ጊዜ በእግሩ ሥር ወደቀችና “ጌታ ሆይ፥ አንተ እዚህ ብትሆን ኖሮ ወንድሜ ባልሞተም ነበር” አለችው።


በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።


እናንተ ‘መምህርና ጌታ’ ትሉኛላችሁ፤ እኔ መምህርና ጌታ ስለ ሆንኩ ያላችሁት ትክክል ነው።


እንግዲህ እኔ ጌታችሁና መምህራችሁ ስሆን እግራችሁን ካጠብኩ እናንተም እርስ በርሳችሁ እግራችሁን መተጣጠብ ይገባችኋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች