Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 42:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 በግብጽ አገር እህል መኖሩን ሰምቼአለሁ፤ በራብ እንዳንሞት ወደዚያ ሂዱና እህል ሸምቱልን” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነሆ፥ እህል በግ​ብፅ እን​ዳለ ሰም​ቼ​አ​ለሁ፤ ወደ​ዚያ ውረዱ፤ እን​ድ​ን​ድ​ንና በራብ እን​ዳ​ን​ሞ​ትም ከዚያ ሸም​ቱ​ልን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 እንዲህም አለ፦ እነሆ ስንዴ በግብፅ እንዲገኝ ሰምቼአለሁ፤ ወደዚይ ውረዱ፥ እንድንድንና እንዳንሞትም ከዚያ ሸምቱልን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 42:2
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ዐሥሩ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ ሄዱ፤


የያዕቆብ ቤተሰብ ከግብጽ የመጣውን እህል ተመግበው በጨረሱ ጊዜ አባታቸው “እንደገና ወደ ግብጽ ሂዱና ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።


ስለዚህ ወንድማችንን ይዘን እንድንሄድ ከፈቀድክልን ሄደን እህል እንሸምትልሃለን።


ይሁዳም አባቱን እንዲህ አለ፤ “ልጁን በእኔ ኀላፊነት አብሮን እንዲሄድ አድርግ፥ ሳንዘገይ አሁኑኑ ጒዞ እንጀምር፤ ይህ ከሆነ፥ እኛም አንተም ልጆቻችንም ሁሉ በራብ ከመሞት እንድናለን።


አሁን በፍጥነት ተመልሳችሁ ወደ አባቴ ሂዱና ልጅህ ዮሴፍ እንዲህ ይልሃል በሉት፤ ‘እግዚአብሔር የመላው ግብጽ ገዢ አድርጎኛል፤ ስለዚህ ሳትዘገይ ወደ እኔ ና፤


በሕይወት እኖራለሁ እንጂ አልሞትም፤ የእግዚአብሔርንም ድንቅ ሥራ ዐውጃለሁ።


እግዚአብሔር የሚፈሩትንና ዘለዓለማዊ ፍቅሩ ተስፋቸው የሆነውን ይመለከታል።


ይህም የሚሆነው ከሞት ሊያድናቸውና ከራብም ሊጠብቃቸው ነው።


በዚያን ዘመን ንጉሥ ሕዝቅያስ በጠና ታሞ ለመሞት ተቃርቦ ነበር፤ የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ሊጐበኘው ወደ እርሱ ሄዶ “እግዚአብሔር ‘ከሕመምህ አትድንም፤ መሞትህም ስለማይቀር ቤትህን አዘጋጅ’ ብሎሃል” ሲል ነገረው።


ኢየሱስ ግን “ ‘ሰው የሚኖረው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ፥ በእንጀራ ብቻ አይደለም’ ተብሎ ተጽፎአል” አለው።


ያዕቆብም በግብጽ እህል መኖሩን በሰማ ጊዜ ለመጀመሪያ ጊዜ አባቶቻችንን ወደዚያ ላከ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች