Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ነገር ግን ወደ ትውልድ አገሬ ሂድ፤ እዚያም ካሉት ወገኖቼ መካከል ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት ምረጥለት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ነገር ግን ወደ አገሬ፣ ወደ ገዛ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ለይሥሐቅ ሚስት ትፈልግለታለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ነገር ግን ወደ ተወ​ለ​ድ​ሁ​በት ወደ ሀገ​ሬና ወደ ተወ​ላ​ጆች ሂድ፤ ለልጄ ለይ​ስ​ሐ​ቅም ከዚያ ሚስ​ትን አም​ጣ​ለት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 24:4
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከዚህ በኋላ 119 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶች ልጆችና ሴቶች ልጆችን ወለደ።


እግዚአብሔር አብራምን እንዲህ አለው፤ “አገርህን ትተህ፥ ከዘመዶችህና ከአባትህ ቤተሰብ ተለይተህ፥ እኔ ወደማሳይህ አገር ሂድ፤


እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።


ነገር ግን ወደ አባቴ ቤት ወደ ወገኖቼ ሄደህ ለልጄ ሚስት ምረጥ፤


አገልጋዩም “ምናልባት የምመርጥለት ሴት ከእኔ ጋር ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገውን?” ብሎ ጠየቀ።


ይስሐቅ ያዕቆብን ጠርቶ መረቀው፤ እንዲህም ሲል አዘዘው፤ “ከነዓናዊት ሴት እንዳታገባ፤


ይልቅስ ተነሥተህ በመስጴጦምያ ወዳለው ወደ እናትህ አባት ወደ ባቱኤል ቤት ሂድ፤ እዚያም ከአጐትህ ከላባ ሴቶች ልጆች አንዷን አግባ፤


ዮዳሄ ለንጉሥ ኢዮአስ ሁለት ሚስቶችን መርጦለት ነበር፤ እነርሱም ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን ወልደውለታል።


ያንን የወጡበትን አገር አስታውሰውት ቢሆኑ ኖሮ ወደዚያ ለመመለስ በቻሉ ነበር።


አባቱና እናቱ ግን “ሚስት ለማግኘት ወደ አልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን ዘንድ ሄደህ ሚስት የምትፈልገው ከወገንህ ወይም በሕዝባችን መካከል ሴት ልጅ የሌለች ሆኖ ነውን?” ሲሉ ጠየቁት። ሶምሶን ግን አባቱን “እኔ እርስዋን በጣም ስለ ወደድኳት ከእርስዋ ጋር አጋባኝ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች