Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 2:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 የቀድሞ አባቶቼ አምላክ ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርግሃለሁ፤ አንተ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛል፤ ጸሎታችንንም ሰምተህ የንጉሡን ሕልም ገልጠህልናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 የአባቶቼ አምላክ ሆይ፤ አመሰግንሃለሁ፤ አከብርሃለሁም፤ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛልና፤ ከአንተ የጠየቅነውን ነገር አሳውቀኸኛል፤ የንጉሡን ሕልም አሳውቀኸናል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ጥበብንና ኃይልን የሰጠኸኝ፥ እኛም የለመንንህን ነገር አሁን ያስታወቅኸኝ፥ አንተ የአባቶቼ አምላክ ሆይ፥ የንጉሡን ነገር አስታውቀኸኛልና እገዛልሃለሁ አመሰግንህማለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 2:23
33 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “እኔ የማደርገውን ነገር ከአብርሃም እሰውረዋለሁን?


አባቴ ይስሐቅ የሚያመልከው የአብርሃም አምላክ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ ባዶ እጄን በሰደድከኝ ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር መከራዬንና ልፋቴን አይቶ ባለፈው ሌሊት ገሥጾሃል።”


ከቀትር በኋላ የሠርክ መሥዋዕት በሚቀርብበት ሰዓት ነቢዩ ኤልያስ ወደ መሠዊያው ቀርቦ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የአብርሃም፥ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የእስራኤል አምላክ መሆንክን፥ እኔም የአንተ አገልጋይ መሆኔን፥ እኔም ይህን ሁሉ ያደረግኹት በቃልህ መሠረት መሆኑን አንተ ራስህ ግለጥ፤


አምላካችን እግዚአብሔር ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር እንደ ነበረ ሁሉ ከእኛ ጋርም ይኑር፤ ምንጊዜም፤ አይተወንም፤ አይጥለንም፤


እዚያም በመላው ጉባኤ ፊት ንጉሥ ዳዊት እግዚአብሔርን አመሰገነ፤ እንዲህም አለ፦ “የቀድሞ አባታችን የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም የተመሰገንክ ሁን!


አሁንም አምላካችን ሆይ፥ ምስጋና እናቀርብልሃለን፤ ክቡር ስምህንም እናወድሳለን።


ድምፁንም ከፍ በማድረግ እንዲህ ሲል ጸለየ፤ “የቀድሞ አባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ በሰማይ ሆነህ የዓለም መንግሥታትን ሁሉ የምታስተዳድር አንተ ነህ፤ ኀይልና ሥልጣን ሁሉ በአንተ እጅ ነው፤ አንተን ሊቋቋምህ የሚችል ማንም የለም፤


የልቡን ምኞት ሰጥተኸዋል፤ የለመነህንም አልከለከልከውም።


ሕይወትን እንድትሰጠው ለመነህ፤ አንተም ረጅም ዕድሜና ዘለዓለማዊ የሆነ ሕይወትን ሰጠኸው።


እግዚአብሔር ለሚታዘዙት ሁሉ ወዳጃቸው ነው፤ ለእነርሱ የገባውንም ቃል ኪዳን ያጸናል።


የምስጋና መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ ስእለትህንም ለልዑል ስጥ።


እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።


ብልኅ የጦር መሪ በብርቱ ሠራዊት የተጠበቀውን ከተማ ድል አድርጎ ይይዛል፤ የተማመኑባቸውንም ምሽጎች ያፈራርሳል።


ብርቱ ከመሆን ይልቅ ብልኅ መሆን ይሻላል፤ በእርግጥም ዕውቀት ከኀይል ይበልጣል፤


ምክርና መልካም ጥበብ ከእኔ ይገኛሉ፤ ማስተዋልና ብርታትም የእኔ ናቸው።


በአንዲት ከተማ ከሚኖሩ ከዐሥር ገዥዎች ይበልጥ ጥበብ ለአስተዋይ ሰው ብርታትን ትሰጠዋለች።


ጥበብ ከኀይል እንደሚበልጥ ተናግሬአለሁ፤ ነገር ግን የድኻ ሰው ጥበብ የተናቀ ነው፤ ለንግግሩም ዋጋ የሚሰጠው የለም።


ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች፤ ነገር ግን አንድ ኃጢአተኛ ብዙ መልካም ነገርን ያጠፋል።


በዚያን ዘመን እንዲህ ብለህ ትዘምራለህ፦ “ጌታ ሆይ! ቀድሞ ተቈጥተኸኝ ነበር፤ አሁን ግን ቊጣህን መልሰህ ስላጽናናኸኝ አመሰግንሃለሁ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ ከአሁን በፊት የማታውቃቸውን ተመርምሮ ሊደረሰባቸው የማይችሉትን ታላላቅ ነገሮች እገልጥልሃለሁ።


እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።


እነርሱም ከቀሩት የባቢሎን ጠቢባን ጋር እንዳይገደሉ የሰማይ አምላክ ምሕረት እንዲያደርግላቸውና ምሥጢሩንም እንዲገልጥላቸው ይለምኑት ዘንድ አሳሰባቸው።


ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ለአገልጋዮቹ ለነቢያት አስቀድሞ ሳይገልጥ ምንም ነገር አያደርግም።


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ነገር ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለአላዋቂዎች ስለ ገለጥክላቸው አመሰግንሃለሁ፤


በዚያን ጊዜ ኢየሱስ በቅዱስ መንፈሱ ተደስቶ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህንን ነገር ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ላልተማሩት ስለ ገለጽክላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎ፥ አባት ሆይ፥ ይህን ለማድረግ የአንተ በጎ ፈቃድ ሆኖአል።


ሰዎቹም ድንጋዩን አነሡት፤ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ላይ ተመልክቶ፥ “አባት ሆይ! ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤


አገልጋይ ጌታው የሚያደርገውን ስለማያውቅ ከእንግዲህ ወዲህ አገልጋዮች አልላችሁም፤ ነገር ግን ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ስለ ገለጥኩላችሁ ወዳጆቼ ብያችኋለሁ፤


ይህ ራእይ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የሚሆነውን ነገር ለአገልጋዮቹ እንዲያሳያቸው እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስም መልአኩን ልኮ ለአገልጋዩ ለዮሐንስ ይህን ራእይ ገለጠለት።


በዚያን ጊዜ ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው ከዳዊት የትውልድ ሐረግ የተነሣ አንበሳ ድል ነሥቶአል፤ እርሱ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍና ሰባቱን ማኅተሞች መክፈት ይችላል” አለኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች