Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 1:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔርም ለእነዚህ ለአራት ወጣቶች በማናቸውም ጥበብና ሥነ ጽሑፍ ዕውቀትና ማስተዋል ሰጣቸው፤ ዳንኤል ግን በተጨማሪ ራእይንና ሕልምን የመተርጐም ችሎታ ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር ለእነዚህ አራት ወጣቶች በማንኛውም ሥነ ጽሑፍና ትምህርት ዕውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፤ ዳንኤልም ማንኛውንም ራእይና ሕልም የመረዳት ችሎታ ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ለእነዚህም ለአራቱ ብላቴኖች እግዚአብሔር በትምህርትና በጥበብ ሁሉ እውቀትንና ማስተዋልን ሰጣቸው፥ ዳንኤልም በራእይና በሕልም ሁሉ አስተዋይ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 1:17
36 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ የጠየቅኸውን አደርጋለሁ፤ እንዲያውም ማንም ሰው ከዚህ በፊት ካገኘውና ወደ ፊትም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ጥበብንና አስተዋይነትን እሰጥሃለሁ፤


እስራኤላውያን ይህን የፍርድ ውሳኔ በሰሙ ጊዜ ሰሎሞን የሕዝብ ጉዳዮችን በትክክለኛ ፍርድ የሚወስንበትን ጥበብ እግዚአብሔር የሰጠው መሆኑን ስለ ተገነዘቡ ታላቅ አክብሮት ሰጡት።


ስለዚህ ሕዝብህን በትክክል ለመምራት የሚያስችለኝን ጥበብና ዕውቀት ስጠኝ፤ ይህ ካልሆነ ግን ታላቅ ሕዝብህን እንዴት ልመራ እችላለሁ?”


ስለዚህ እነሆ የጠየቅኸውን ጥበብና ዕውቀት እሰጥሃለሁ፤ በተጨማሪም ከዚህ በፊት ማንም ንጉሥ ካገኘውና ወደፊትም ማንም ሊያገኘው ከሚችለው የሚበልጥ ብልጽግና፥ ሀብትና ዝና እሰጥሃለሁ።”


መንፈሳዊ አማካሪው ዘካርያስ በሕይወት እስከ ነበረበት ዘመን ድረስ ዖዝያ እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለግል ነበር፤ እግዚአብሔርም ባረከው።


ነገር ግን በሰው ዐድሮ ጥበብን የሚሰጥ የልዑል እግዚአብሔር መንፈስ ነው።


ጥበብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ ዕውቀትና ማስተዋልም የሚገኙት ከእርሱ ዘንድ ነው።


እግዚአብሔር ደስ ለሚያሰኘው ሰው ብቻ ጥበብን፥ ዕውቀትንና ደስታን ይሰጠዋል፤ ለኃጢአተኛ ሰው ግን ድካምን ብቻ ያተርፍለታል፤ ስለዚህም እርሱ ያከማቸውን ሀብት ሁሉ ምንም ላልደከመበት እግዚአብሔርን ደስ ለሚያሰኝ ለሌላ ሰው ትቶለት እንዲያልፍ ያደርገዋል፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።


ከአምላኩ የተማረ ስለ ሆነ ትክክለኛውን መንገድ ያውቃል።


ከዳንኤል ይበልጥ ጥበበኛ የሆንክ ይመስልሃል፤ ምንም ምሥጢር እንደማይሰወርብህም ታስባለህ፤


ንጉሡ የወሰነው ሦስት ዓመት ሲፈጸም አሽፈናዝ ወጣቶቹን ሁሉ ወስዶ በናቡከደነፆር ፊት አቀረባቸው።


ጥበብና ማስተዋልን በተመለከቱ ጉዳዮች ንጉሡ በሚጠይቃቸው ነገሮች በንጉሠ ነገሥቱ ግዛት ከሚገኙ ጠንቋዮችና አስማተኞች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ብልጫ ያላቸው ሆነው አገኛቸው።


የሚመረጡትም ወጣቶች በቤተ መንግሥት ለማገልገል በቂ ችሎታ እንዲኖራቸው፥ መልከ መልካሞች፥ ጥበብን ሁሉ ማስተዋልና ሁሉን ነገር በፍጥነት መረዳት የሚችሉ፥ የአካል ጒድለት የሌለባቸው መሆን ይገባቸዋል፤ እንዲሁም የባቢሎናውያንን ቋንቋና ሥነ ጽሑፍ ያስተምራቸውም ዘንድ አዘዘው።


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ብልጣሶር ለተባለው ለዳንኤል ሌላ ራእይ ተገለጠለት፤ በራእዩም የተነገረው ቃል እውነት ነው፤ ነገር ግን ለማስተዋል እጅግ ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ትርጒሙ በራእይ ተገለጠለት።


በዚያኑ ሌሊት ምሥጢሩ ለዳንኤል በራእይ ተገለጠለት፤ ስለዚህ የሰማይን አምላክ እንዲህ ሲል አመሰገነ፦


እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው።


የቀድሞ አባቶቼ አምላክ ሆይ! አመሰግንሃለሁ፤ ከፍ ከፍም አደርግሃለሁ፤ አንተ ጥበብንና ኀይልን ሰጥተኸኛል፤ ጸሎታችንንም ሰምተህ የንጉሡን ሕልም ገልጠህልናል።”


ይህም ምሥጢር ለእኔ የተገለጠልኝ ከሌሎች ሰዎች ይልቅ ጥበበኛ ስለ ሆንኩ አይደለም፤ ነገር ግን አንተ የሕልሙን ትርጒም እንድታውቅና በአእምሮህም ውስጥ የተመላለሰውን ሐሳብ መረዳት እንድትችል ነው።


ስለዚህ የሕልሙን ትርጒም እንዲነግሩኝ በባቢሎን የሚገኙትን ጠቢባን ሁሉ ወደ እኔ እንዲመጡ አደረግሁ።


የቅዱሳን አማልክት መንፈስ በአንተ እንዳለና ብልኀት፥ ዕውቀትና ጥበብ የተሰጠህ መሆኑን ሰምቼአለሁ።


የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር በነገሠ በመጀመሪያው ዓመት በአልጋው ላይ ተኝቶ ሳለ፤ ዳንኤል ሕልምና ራእይ አየ፤ ከዚያም በኋላ ያየውን ሕልም ጻፈ።


ብልጣሶር በነገሠ በሦስተኛው ዓመት እኔ ዳንኤል ከዚህ በፊት ካየሁት ሌላ ራእይ አየሁ፤


እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤


ከጠላቶቻችሁ ማንም ሊቋቋመው ወይም ሊቃወመው የማይችለውን አንደበትና ጥበብ እኔ እሰጣችኋለሁ።


ነገር ግን እስጢፋኖስ ይናገርበት የነበረውን ጥበብና መንፈስ መቋቋም አልቻሉም።


ከመከራው ሁሉ አወጣው፤ በግብጽ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው። ንጉሡም በግብጽና በቤቱም ሁሉ ላይ አዛዥ አደረገው።


ሙሴም የግብጻውያንን ጥበብ ሁሉ ተማረ፤ በቃሉና በሥራውም የበረታ ሆነ።


ስለዚህ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምሮ እናንተ በመንፈሳዊ ጥበብና ማስተዋል ሁሉ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምትገነዘቡበት ሙሉ ዕውቀት እንዲኖራችሁ ለእናንተ ከመጸለይና እግዚአብሔርን ከመለመን አላቋረጥንም።


መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።


ከእናንተ መካከል ጥበብ የጐደለው ሰው ቢኖር እግዚአብሔርን ይለምን፤ እግዚአብሔርም ይሰጠዋል፤ እርሱ ምንም ቅር ሳይለው ለሁሉም በልግሥና የሚሰጥ ቸር አምላክ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች