Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዳንኤል 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ ዳንኤል ራሱንና ጓደኞቹን ሐናንያን፥ ሚሳኤልንና አዛርያን እንዲጠብቅ አሽፈናዝ ወደ መደበው ጠባቂ ሄዶ እንዲህ አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ዳንኤልም የጃንደረቦቹን አለቃ በዳንኤል፣ በአናንያ፣ በሚሳኤልና በአዛርያስ ላይ የሾመውን መጋቢ እንዲህ አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ዳንኤልም የጃንደርቦቹ አለቃ በዳንኤልና በአናንያ በሚሳኤልና በአዛርያ ላይ የሾመውን ሜልዳርን፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዳንኤል 1:11
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁን እንጂ ንጉሡን ስለ ፈራ አሽፈናዝ ዳንኤልን “ምግባችሁንና መጠጣችሁን ያዘዘ ንጉሡ ራሱ ነው፤ እናንተ ከሌሎቹ ወጣቶች ይልቅ ከስታችሁና ተጐሳቊላችሁ ብትገኙ ጌታዬ ንጉሡ በሞት ይቀጣኛል ብዬ እፈራለሁ” አለው።


“አትክልት እየተመገብንና ውሃ እየጠጣን እንድንቈይ በማድረግ እኛን አገልጋዮችህን ለዐሥር ቀን ያኽል ፈትነን፤


ከዚያን ጊዜ አንሥቶ ጠባቂው ከቤተ መንግሥት የሚላክላቸውን ምርጥ ምግብና የወይን ጠጅ አስቀርቶ ለእነርሱ የአትክልት ምግብ ይሰጣቸው ጀመር።


ከዚህ በኋላ ዳንኤል ወደ ቤቱ ሄደና የሆነውን ነገር ለጓደኞቹ ለሐናንያ፥ ለሚሳኤልና ለዐዛርያ ነገራቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች