2 ሳሙኤል 24:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም20 ኦርናም ወደ ታች ሲመለከት ንጉሥ ዳዊትና ባለሟሎቹ የሆኑት ባለሥልጣኖች ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ እርሱም በዳዊት ፊት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም20 ኦርናም ቀና ብሎ ንጉሡና ሰዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ መሬት ለጥ ብሎ ለንጉሡ እጅ ነሣ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)20 ኦርናም ቁልቁል ሲመለከት፥ ንጉሡና አገልጋዮቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፋ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ኦርናም ሲመለከት ንጉሡና ብላቴናዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፤ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ሰገደ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)20 ኦርናም ሲመለከት ንጉሡና ባሪያዎቹ ወደ እርሱ ሲመጡ አየ፥ ኦርናም ወጥቶ በንጉሡ ፊት በምድር ላይ በግምባሩ ተደፋ። ምዕራፉን ተመልከት |