Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 14:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የምነግርህን አድምጠህ ልጄንና እኔን በማጥፋት እግዚአብሔር የራሱ ካደረገው ምድር ሊያስወግደን ከሚፈልገው ሰው ታድነኛለህ ብዬ አስቤ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እግዚአብሔር ከሰጠን ርስት እኔንም ልጄንም ሊነቅለን ከተነሣው ሰው እጅ ንጉሡ አገልጋዩን ሊታደግ ይፈቅድ ይሆናል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ‘እግዚአብሔር ከሰጠን ርስት እኔንም ልጄንም ሊያጠፋን ከተነሣው ሰው እጅ ንጉሡ አገልጋዩን ሊታደግ ይፈቅድ ይሆናል።’

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እኔ​ንና ልጄን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት ያር​ቀን ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ አገ​ል​ጋ​ዩን ይሰ​ማል አልሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እርስዋንና ልጅዋን ከእግዚአብሔር ርስት ያጠፋቸው ዘንድ ከሚሻ ሰው እጅ ያድን ዘንድ ንጉሡ ባሪያውን ይሰማል አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 14:16
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁንም ንጉሥ ሆይ፥ እኔ ወደ አንተ የመጣሁት በዚህ ነገር ሰዎች ያስፈራሩኝ መሆኑን ልነግርህ ነው፤ ‘የጠየቅሁትን ሁሉ ያደርግልኛል’ በሚል ተስፋም በፊትህ ቀርቤአለሁ፤


የእኔ ከተማ ግን ታላቅ ከተማ ናት፤ በእስራኤል ሰላም የሰፈነባትና ታማኝ ከተማ እርስዋ ናት፤ ታዲያ፥ አንተ ይህችን ከተማ ለመደምሰስ ለምን ታቅዳለህ? የእግዚአብሔር ርስት የሆነውን ነገር ለማፍረስ ትፈልጋለህን?”


ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች፥ ችግረኞችንና የተጨቈኑትን ሰዎች ነጻ ያወጣል።


ንጉሥ የሚፈርደው ከእግዚአብሔር በተቀበለው ሥልጣን ነው፤ ስለዚህ ውሳኔዎቹ ዘወትር ትክክል ናቸው።


እስራኤል የእግዚአብሔር ድርሻ ነው፤ ያዕቆብም አንጡራ ሀብቱ ነው።


ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች