Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




2 ሳሙኤል 11:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 ከዚያም በኋላ በግንብ ላይ ሆነው ፍላጻዎችን ወረወሩብን፤ ንጉሥ ሆይ! ከጦር መኰንኖችህ ጥቂቶቹ በዚያን ጊዜ ሞቱ፤ አገልጋይህ ኦርዮም ተገደለ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ከዚያም ባለፍላጻዎቹ ከግንቡ ላይ ሆነው በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ስለ ለቀቁ፣ ከንጉሡ አገልጋዮች ጥቂቶቹን ገደሉ፤ አገልጋይህ ኬጢያዊው ኦርዮም ሞተ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ከዚያም ባለፍላጻዎቹ ከግንቡ ላይ ሆነው በእኛ በአገልጋዮችህ ላይ ቀስት ስለ ለቀቁ፥ ከንጉሡ አገልጋዮች ጥቂቶቹን ገደሉ፤ አገልጋይህ ሒታዊው ኦርዮም ሞተ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ፍላ​ጻም የሚ​ወ​ረ​ውሩ በቅ​ጥሩ ላይ ሆነው በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ ላይ ወረ​ወሩ፤ ከን​ጉ​ሡም ብላ​ቴ​ኖች አን​ዳ​ንድ ሞቱ፤ አገ​ል​ጋ​ይህ ኬጤ​ያ​ዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ፍላጻ የሚወረውሩም በቅጥሩ ላይ ሆነው በባሪያዎችህ ላይ ወረወሩ፥ ከንጉሡም ባሪያዎች አንዳንድ ሞቱ፥ ባሪያህም ኬጢያዊው ኦርዮ ደግሞ ሞተ አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ሳሙኤል 11:24
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ጠላቶቻችን ስለ በረቱብን እኛን ለመውጋት ከከተማይቱ ወጥተው ወደ ሜዳ መጡ፤ እኛ ግን አሳደን ወደ ከተማይቱ ቅጽር በር መለስናቸው።


ዳዊትም መልእክተኛውን “እንዲህ ብለህ ለኢዮአብ ንገረው፦ በጦርነት ላይ ማን እንደሚሞት በቅድሚያ ስለማይታወቅ ‘አይዞህ በርታ’ በለው፤ ብስጭት እንዳያድርበትም ንገረው፤ ይልቁንም ኀይሉን አጠናክሮ አደጋ በመጣል ከተማይቱን እንዲይዝ አስጠንቅቀው” አለው።


ስለዚህ ዘሮቻቸው ተደመሰሱ ከሐሴቦን እስከ ዲቦን፥ እሳቱ እስከ ሜዴባ እስኪስፋፋ ድረስ አጠፋናቸው።”


ከዚህም በኋላ ዳዊት ሒታዊውን አቤሜሌክንና ከጸሩያ ልጆች የኢዮአብን ወንድም አቢሳን “ከእናንተ ከሁለታችሁ ከእኔ ጋር አብሮ ወደ ሳኦል ሰፈር የሚሄድ ማን ነው?” ሲል ጠየቃቸው። አቢሻይም “እኔ እሄዳለሁ” ሲል መለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች