Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 31:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ከጦርነቱ ቀጥሎ ባለው ቀን ፍልስጥኤማውያን የሟቾቹን ሬሳ ትጥቅ ለመግፈፍ ሄደው ሳኦልንና ሦስቱን ልጆቹን በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በማግስቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 በማግስቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ሰዎች ለመግፈፍ ሲመጡ፥ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገቿቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በማ​ግ​ሥ​ቱም ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን የሞ​ቱ​ትን ለመ​ግ​ፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦ​ልና ሦስቱ ልጆቹ በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወድ​ቀው አገ​ኙ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በማግሥቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልና ሦስቱ ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 31:8
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች እንዳይደሰቱ፥ የአሕዛብ ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ ይህን ወሬ በጋት አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ አታውጁ።


“እናንተ የጊልቦዓ ተራራዎች ሆይ! ዝንብም ሆነ ጤዛ አይውረድባችሁ! የእርሻ መሬቶቻችሁም ምንም ነገር አይብቀልባቸው! የጀግኖች ጋሻዎች እዚያ በውርደት ወድቀዋልና፤ የሳኦልም ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና።


በጦርነቱ ማግስት ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን እስራኤላውያን ለመግፈፍ በሄዱ ጊዜ የሳኦልና የልጆቹ ሬሳ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተጋድሞ አገኙ፤


ከዚህ በኋላ ኢዮሣፍጥና ወታደሮቹ ምርኮ ለመውሰድ ወደዚያ ሄዱ፤ ብዙ የቀንድ ከብት፥ ስንቅና ትጥቅ፥ ልብስና ሌላም ውድ የሆኑ ዕቃዎች አገኙ፤ ምርኮውንም ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀባቸው፤ ነገር ግን ምርኮው እጅግ ብዙ ስለ ነበር ሁሉንም መውሰድ አልቻሉም፤


የፍልስጥኤም ወታደሮች ተሰልፈው መጥተው በሹኔም ከተማ አጠገብ ሰፈሩ፤ ሳኦልም እስራኤላውያንን አሰልፎ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ሰፈረ፤


ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምሥራቅና በኢይዝራኤል ሸለቆ ማዶ የነበሩ እስራኤላውያንም የእስራኤል ሠራዊት መሸሹን፥ ሳኦልና ልጆቹም መገደላቸውን ሰምተው ከተሞቻቸውን እየጣሉ ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቹን ያዙ።


የሳኦልንም ራስ ቈርጠው የጦር ልብሱንም ገፈው በማስያዝ ለአማልክቶቻቸው መቅደስና ለሕዝባቸው የድሉን ዜና ያበሥሩ ዘንድ መልእክተኞቻቸውን ላኩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች