Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 24:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ጠላት በእጁ ገብቶለት ጒዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ሰው ከቶ የት ይገኛል? ዛሬ ለእኔ ስላደረግኸው መልካም ነገር እግዚአብሔር ይባርክህ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ለመሆኑ ጠላቱን አግኝቶ ጕዳት ሳያደርስበት የሚለቀው ማን ነው? ዛሬ ስላደረግህልኝ ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ያደረግህልኝን በጎ ነገር ይኸው ነግረኸኛል፤ ጌታ እኔን በእጅህ ቢጥልልህም አንተ ግን አልገደልኸኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዛሬ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶኝ ሳለ አል​ገ​ደ​ል​ኸ​ኝ​ምና ለእኔ መል​ካም እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ኽ​ልኝ ለእኔ ነገ​ር​ኸኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ጠላቱን አግኝቶ በመልካም መንገድ ሸኝቶ የሚሰድድ ማን ነው? ስለዚህ ለእኔ ስላደረግኸው ቸርነት እግዚአብሔር ይመልስልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 24:19
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄም ንጽሕና ይመልስልኛል።


እርሱም አንድ ቀን እናቱን እንዲህ አላት፤ “አንድ ሰው አንድ ሺህ አንድ መቶ ጥሬ ብር በሰረቀሽ ጊዜ ያን የሰረቀሽን ሰው ስትረግሚው ሰምቼሽ ነበር፤ እነሆ ያ ብር በእኔ እጅ ነው፤ እርሱንም የወሰድኩ እኔ ነበርኩ።” እናቱም “ልጄ! እግዚአብሔር ይባርክህ!” አለችው።


እግዚአብሔር ላደረግሽው በጎ ነገር ዋጋሽን ይክፈልሽ! የእርሱን ጥበቃ ተማምነሽ የመጣሽው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ዋጋሽን የተትረፈረፈ ያድርገው!”


“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”


ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰላቸው፤ “ለእኔ ይህን ያኽል ቸርነት ስላደረጋችሁልኝ እግዚአብሔር ይባርካችሁ!


ታማኞች ለሆኑ ለደጋግ ሰዎች የመልካም ሥራቸውን ዋጋ የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው፤ እነሆ፥ ዛሬ እግዚአብሔር አንተን በእጄ ጥሎልኝ ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔር መርጦ ያነገሠህን አንተን ልጐዳ አልፈለግሁም።


ሳኦልም ዳዊትን “ልጄ ሆይ፥ እግዚአብሔር ይባርክህ! ብዙ ነገርን ታደርጋለህ፤ ይሳካልሃልም” አለው። ስለዚህም ዳዊት ወደ ፈለገበት ቦታ ሄደ፤ ሳኦልም ወደ ቤቱ ተመለሰ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች