Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 20:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14-15 በሕይወት ብኖር እግዚአብሔር የሚወድደውን ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤ ብሞት ግን እግዚአብሔር የአንተን የዳዊትን ጠላቶች ሁሉ ከገጸ ምድር በሚያጠፋበት ጊዜ ታማኝ የሆነውን ፍቅርህን ከቤተሰቤም አታቋርጥ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አንተም እኔ በሕይወት እስካለሁ ድረስ እንዳልገደል የእግዚአብሔርን በጎነት አድርግልኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እኔም እንዳልሞት፥ በሕይወት እስካለሁ የጌታን ታማኝ ፍቅር አሳየኝ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እኔም በሕ​ይ​ወት ሳለሁ ቸር​ነ​ትን ታደ​ር​ግ​ል​ኛ​ለህ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እኔም እንዳልሞት በሕይወቴ ዘመን የእግዚአብሔርን ቸርነት አድርግልኝ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 20:14
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነገር ግን ሁሉ ነገር በተቃናልህ ጊዜ እኔን አስታውሰህ እርዳኝ፤ ለፈርዖንም አሳስበህ ከእዚህ ከእስር ቤት እንድወጣ አድርገኝ።


አንድ ቀን ዳዊት “ስለ ዮናታን ስል ቸርነት እንዳደርግለት ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ብሎ ጠየቀ።


ንጉሡም “እግዚአብሔር የሚፈቅደውን ቸርነት የማሳየው ከሳኦል ቤተሰብ ከሞት የተረፈ ሰው አለን?” ሲል ጺባን ጠየቀው። ጺባም “ከዮናታን ወንዶች ልጆች አንዱ አሁንም በሕይወት አለ፤ እርሱም እግረ ሽባ ነው” ሲል መለሰ።


አንተን ለመጒዳት የሚፈልግ ከሆነ ግን፥ ስለ እርሱ ባልገልጥልህና አንተም በሰላም እንድታመልጥ ባላደርግ አባቴ በአንተ ላይ ሊያደርግ ያሰበውን ክፉ ነገር እግዚአብሔር በእኔ ላይ ያድርሰው። እግዚአብሔር ከአባቴ ጋር እንደ ነበር ከአንተም ጋር ይሁን፤


እርስ በርሳችን የገባነውን ቃል ኪዳን ለዘለዓለም እንደምንጠብቀው እግዚአብሔር ምስክራችን ነው። ”


እንግዲህ ስሜና የቤተሰቤ ስም ተደምስሶ እንዳይረሳ ለማድረግና የዘሮቼንም ሕይወት ከጥፋት ለማትረፍ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች