Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚህ በኋላ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ለመሄድ ተነሣ፤ እዚያም ሴኩ በሚባለው ስፍራ ወደሚገኘው ወደ አንድ ታላቅ የውሃ ጒድጓድ በደረሰ ጊዜ “ሳሙኤልና ዳዊት የሚገኙት የት ነው?” ብሎ ቢጠይቅ፥ በናዮት መኖራቸው ተነገረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 በመጨረሻም፣ እርሱ ራሱ ወደ አርማቴም ሄደ፤ ከዚያም በሤኩ ወዳለው ትልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ እንደ ደረሰ፣ “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። አንድ ሰውም “በአርማቴም በምትገኘው በነዋት ዘራማ ናቸው” ብሎ ነገረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በመጨረሻም፥ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ሄደ፤ ከዚያም በሴኩ ወዳለው ትልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንደ ደረሰ፥ “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። አንድ ሰውም “በራማ በምትገኘው የራማዋ ናዮት ናቸው” ብሎ ነገረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሳኦ​ልም እጅግ ተቈጣ፤ እር​ሱም ደግሞ ወደ አር​ማ​ቴም መጣ፤ በመ​ሴ​ፋም አው​ድማ ወዳ​ለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድ​ጓድ ደረሰ። “ሳሙ​ኤ​ልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአ​ው​ቴ​ዘ​ራማ ናቸው” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የሳኦልም ቁጣ ነደደ፥ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፥ በሤኩም ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው? ብሎ ጠየቀ፥ አንድ ሰውም፦ እነሆ፥ በአርማቴም አገር በነዋትዘራማ ናቸው አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 19:22
3 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም አምልጦ ሳሙኤል ወደነበረበት ወደ ራማ መጣ፤ ሳኦል ያደረገበትንም በደል ሁሉ ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤልና ዳዊት በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ፤


ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም እንደዚያው ትንቢት መናገር ቀጠሉ፤ ሳኦልም ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ቢልክ ያው ነገር በእነርሱም ላይ ተደገመ፤


ወደዚያም በማምራት ላይ ሳለ የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱም ላይ ወረደበት፤ እስከ ናዮት በሚያደርሰው መንገድ ሁሉ ትንቢት ይናገር ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች