Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 16:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከዚያም በኋላ ሳኦል ወደ እሴይ መልእክት ልኮ “ዳዊትን ወድጄዋለሁ፤ ስለዚህ እዚህ በመቈየት ያገልግለኝ” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዚያም ሳኦል፣ “ዳዊትን ወድጄዋለሁና ከእኔ ዘንድ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ፍቀድልኝ” ብሎ ወደ እሴይ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዚያም ሳኦል፥ “ዳዊትን ወድጄዋለሁና ከእኔ ዘንድ ሆኖ እንዲያገለግለኝ ፍቀድልኝ” ብሎ ወደ እሴይ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ሳኦ​ልም ወደ እሴይ፥ “በዐ​ይኔ ሞገስ አግ​ኝ​ቶ​አ​ልና ዳዊት በፊቴ እባ​ክህ ይቁም፥” ብሎ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ሳኦልም ወደ እሴይ፦ በዓይኔ ሞገስ አግኝቶአልና ዳዊት በፊቴ፥ እባክህ፥ ይቁም ብሎ ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 16:22
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ላባም “በልዩ መገለጥ እንደ ተረዳሁት በአንተ ምክንያት እግዚአብሔር የባረከኝ መሆኑን እንድገልጽልህ ፍቀድልኝ፤


ጶጢፋር ዮሴፍን ወደደው፤ የቅርብ አገልጋዩም አደረገው፤ በቤቱ ላይ አዛዥነትን፥ በንብረቱም ሁሉ ላይ ኀላፊነትን ሰጠው።


እግዚአብሔር ሆይ! ልቤ በኩራት የተወጠረ አይደለም፤ ዐይኖቼም ትዕቢተኞች አይደሉም፤ ስለ ታላላቅ ነገሮች ወይም ላስተውለው ስለማልችለው ከባድ ነገር አልጨነቅም።


ምግባቸውና የሚጠጡት የወይን ጠጅ ከንጉሡ ማእድ እንዲሆን ታዘዘላቸው፤ በዚህ ዐይነት ለሦስት ዓመት ከሠለጠኑ በኋላ በንጉሡ ፊት ቀርበው የቤተ መንግሥት ሥራቸውን እንዲጀምሩ ተወሰነ።


ነገር ግን የአንተ ረዳት የሆነው የነዌ ልጅ ኢያሱ ወደ ምድሪቱ ይገባል፤ ምድሪቱን ይወርሱ ዘንድ እስራኤልን የሚመራ እርሱ ስለ ሆነ አበረታታው።’


ዳዊትም ወደ ሳኦል መጥቶ ሥራውን ጀመረ፤ ሳኦልም በጣም ስለ ወደደው የእርሱ መሣሪያ ያዥ ጋሻጃግሬ አደረገው።


ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ከእግዚአብሔር የተላከ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ ዳዊት በገናውን አንሥቶ ይደረድራል፤ ክፉውም መንፈስ ለቆት ስለሚሄድ ሳኦል እየተሻለው እንደገና ጤናማ ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች