Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 16:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እሴይም ዳዊትን አንድ ትንሽ የፍየል ጠቦት አስይዞ፥ እንጀራና የወይን ጠጅ የተሞላበት አቁማዳ ከተጫነ አንድ አህያ ጋር ወደ ሳኦል ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 እሴይም እንጀራና በወይን ጠጅ የተሞላ አቍማዳ በአህያ አስጭኖ፣ የፍየል ጠቦትም አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 እሴይም እንጀራና በወይን ጠጅ የተሞላ አቁማዳ በአህያ አስጭኖ፥ የፍየል ጠቦትም አስይዞ ልጁን ዳዊትን ወደ ሳኦል ላከው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 እሴ​ይም እን​ጀ​ራና የወ​ይን ጠጅ አቁ​ማዳ የተ​ጫነ አህያ፥ አን​ድም የፍ​የል ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳ​ዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 እሴይም እንጀራና የወይን ጠጅ አቁማዳ የተጫነ አህያ የፍየልም ጠቦት ወስዶ በልጁ በዳዊት እጅ ወደ ሳኦል ላከ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 16:20
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባታቸው ያዕቆብም እንዲህ አላቸው፤ “እንግዲህ መሄዳችሁ የማይቀር ከሆነ ለአገረ ገዢው ገጸ በረከት የሚሆን ምድራችን ከምታፈራው ምርጥ ነገር ሁሉ በስልቻዎቻችሁ ጨምራችሁ ሂዱ፤ ይኸውም በለሳን፥ ማር፥ ቅመማ ቅመም፥ ከርቤ፥ ተምርና ለውዝ ይዛችሁ ሂዱ።


ስጦታ ለሰጪው መንገድን ይከፍትለታል፤ ወደ ትልልቆች ሰዎችም ፊት መቅረብ ያስችለዋል።


ነገር ግን አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች “አሁን ይህ ሰው እኛን ለማዳን ይችላል?” ተባባሉ፤ እርሱንም በመናቅ ምንም ዐይነት ገጸ በረከት ሳያመጡለት ቀሩ። ሳኦል ግን ዝም አለ።


እነርሱም ሰላምታ ከሰጡህ በኋላ ከኅብስቶቹ ሁለቱን ይሰጡሃል፤ አንተም መቀበል ይገባሃል፤


ስለዚህም ሳኦል ወደ እሴይ መልእክተኞች ልኮ “የበጎች እረኛ የሆነውን ልጅህን ዳዊትን ላክልኝ” አለው።


እነዚህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃው የጦር አዛዥ ስጠው፤ ወንድሞችህም እንዴት እንዳሉ በዐይንህ አይተህ የደኅንነታቸውን መረጃ አምጣልኝ።


አቢጌልም በፍጥነት ሁለት መቶ እንጀራ፥ ወይን ጠጅ የተሞላበት ሁለት የወይን አቁማዳ፥ አምስት የተጠበሱ በጎች፥ ዐሥራ ሰባት ኪሎ የተጠበሰ እሸት፥ አንድ መቶ ዘለላ ወይንና ሁለት መቶ የበለስ ፍሬ ጥፍጥፍ በአንድነት ሰብስባ በአህዮች ላይ ጫነች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች