Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ መሸጉ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮችም ምሽግ በሚክማስ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ፍልስጥኤማውያን በማክማስ ሰፍረው በነበረበት ጊዜ ሳኦል፣ ልጁ ዮናታንና ዐብረዋቸው የነበሩት ሰዎች በብንያም ግዛት በምትገኘው በጌባዕ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ ነበሩ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች ግን በሚክማስ ሰፍረው ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ሳኦ​ልና ልጁ ዮና​ታ​ንም፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ሕዝብ በብ​ን​ያም ገባ​ዖን ተቀ​ም​ጠው አለ​ቀሱ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም በማ​ኪ​ማስ ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ሳኦልና ልጁ ዮናታንም ከእርሱም ጋር የነበሩ ሕዝብ በብንያም ጊብዓ ተቀመጡ፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ ሰፈሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:16
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መተላለፊያውን አልፈው ዐዳር በጌባዕ ሆነ በራማ ከተማ የሚኖሩ ሁሉ ደነገጡ፤ በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ የሚኖሩትም ሁሉ ሸሹ።


ከእስራኤል ሕዝብ መካከል የተውጣጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን መረጠ፤ ከእነርሱ መካከል ሁለቱን ሺህ በሚክማስና በቤትኤል በሚገኘው ኮረብታማ አገር ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ መደበ፤ አንዱን ሺህ ሰዎች ደግሞ ከልጁ ከዮናታን ጋር በማሰለፍ በብንያም ነገድ ግዛት ውስጥ ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ኮረብታማ አገር ላከ፤ ከዚህ የተረፉትን ሌሎች ሰዎች ግን ወደየቤታቸው አሰናበተ።


ዮናታን ጌባዕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ይህን ወሬ ሰሙ፤ ሳኦልም መልእክተኞችን ልኮ በሀገሩ ሁሉ እምቢልታ በማስነፋት ዕብራውያን ለጦርነት ጠራ።


በዚህ ጊዜ ሳኦል ከጊብዓ በጣም ሳይርቅ በሚግሮን በአንድ የሮማን ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር፤ ከእርሱም ጋር ስድስት መቶ ያኽል ጭፍሮች ነበሩ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች