ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጥበብ 14:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ሐውልቶች ይመለኩ ዘንድ ያዘዙ ገዢዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ ርቀው የሚኖሩ በመሆናቸው በግንባር አክብሮታቸውን መግለጽ ላልቻሉት ሁሉ፥ የሚያከብሩትን ንጉሥ ምስል ያዩ ዘንድ፥ የገጽታው ንድፍ ተሠርቶ ይቀርብላቸው ነበር። ዓላማውም ከዓይነ የራቀውን በቅርብ እንዳለ ማስመሰል ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 በሩቅ ስለሚኖሩ ፊት ለፊት ሊያከብሯቸው የማይቻላቸውን ሰዎች ቅርፁ በሩቅ ያለ መልካቸውን ቀረፁ፥ በእነርሱ ዘንድ ክቡር ለሚሆን ለንጉሡም ግልጥ የሆነ ምስል ሠሩለት። የሌለውንም እንዳለ አድርገው በትጋት ይለምናሉ። ምዕራፉን ተመልከት |