ሮሜ 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 “እኔ ሕያው ነኝ፤” ይላል ጌታ፤ “ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ልሳንም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤” ተብሎ ተጽፎአልና። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ ‘እኔ ሕያው ነኝና’ ይላል ጌታ፤ ‘ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይመሰክራል።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ምክንያቱም፦ “እኔ ሕያው ነኝ ይላል እግዚአብሔር፤ ሰው ሁሉ በጒልበቱ በእኔ ፊት ይንበረከካል፤ በአንደበቱም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ይመሰክራል” ተብሎ ተጽፎአል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአልና፥ “እኔ ሕያው ነኝ፤ ጕልበትም ሁሉ ለእኔ ይሰግዳል፤ አንደበትም ሁሉ ለእኔ ይገዛል።” ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እኔ ሕያው ነኝ፥ ይላል ጌታ፥ ጉልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል መላስም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናል ተብሎ ተጽፎአልና። ምዕራፉን ተመልከት |