Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ራእይ 18:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርሷ ዘንድ ውጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከዚያም ከሰማይ ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ፤ በኀጢአቷ እንዳትተባበሩ፤ ከመቅሠፍቷም እንዳትካፈሉ፤ ከርሷ ውጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሌላ ድምፅም ከሰማይ እንዲህ ሲል ሰማሁ፤ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ፤ የመቅሠፍትዋም ተካፋዮች እንዳትሆኑ፤ ከእርስዋ ውጡ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል፦ ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ራእይ 18:4
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም፦ ተነሡ፥ ከዚህ ስፍራ ውጡ፥ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። አማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።


ሌባውን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ጋር ትሮጥ ነበር እድል ፈንታህንም ከአመንዝሮች ጋር አደረግህ።


ከባቢሎን ውጡ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፥ ይህንንም ንገሩ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩ፦ “ጌታ ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል!” በሉ።


እናንተ የጌታን ዕቃ የምትሸከሙ ሆይ፥ እልፍ፥ እልፍ በሉ፥ ከዚያ ውጡ፥ ርኩስን ነገር አትንኩ፥ ከመካከልዋ ውጡ፥ ንጹሐን ሁኑ።


ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።


ሕዝቤ ሆይ! ከመካከልዋ ውጡ እያንዳንዱም ሰው ከጌታ ጽኑ ቁጣ ነፍሱን ያድን።


ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ! ሂዱ፥ አትቁሙ፤ በሩቅ ስፍራ ሆናችሁ ጌታን አስታውሱ፥ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡአት።


ከባቢሎን ውስጥ ሽሹ፥ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፥ የጌታ የበቀል ጊዜ በእርሷ ላይ ነውና፥ እርሱም ብድራትዋን ይከፍላታልና።


ባቢሎንን ልንፈውሳት ሞከርን፥ እርሷ ግን አልተፈወሰችም፤ ፍርድዋ እስከ ሰማይ ደርሶአልና፥ እስከ ደመናም ድረስ ከፍ ከፍ ብሏልና ትታችኋት እያንዳንዳችን ወደ አገራችን እንሂድ።


‘በአባቶቻችን ዘመን ኖረን ቢሆን ኖሮ በነቢያት ደም ባልተባበርናቸውም ነበር’ ትላላችሁ።


ስለዚህም ጌታ ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ፤ ርኩስንም አትንኩ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥


በማንም ላይ ፈጥነህ እጆችህን አትጫን፤ በሌሎችም ኃጢአት አትተባበር፤ ራስህን በንጽህና ጠብቅ።


ሰላም የሚለው የክፉ ሥራው ተካፋይ ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች