Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 59:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እግዚአብሔር መጠጊያዬ ነውና ኃይሌን ወደ አንተ አስጠጋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር በምሕረቱ ይገናኘኛል፤ አምላኬ የጠላቶቼን ውድቀት ያሳየኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 አምላኬ በዘለዓለማዊ ፍቅሩ በፊቴ ይሄዳል፤ ጌታዬ፥ ጠላቶቼን በንቀት ዐይን እንድመለከታቸው ያደርገኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 አቤቱ፥ የጣ​ል​ኸን አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን? አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ችን ጋር አት​ወ​ጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 59:10
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊትም በሳኦልና በልጁ በዮናታን ሞት ምክንያት ይህን የኀዘን እንጉርጉሮ ተቀኘ፤


በጠላቶቹ ላይ እስኪኮራ ድረስ ልቡ ጽኑ ነው፥ አይፈራምም።


የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።


የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


እኔ ግን በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፥ አንተን በመፍራት ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።


እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥ ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።


ክፋትን ወደ ጠላቶቼ ይመልሳታል፥ በእውነትህም አጥፋቸው።


አቤቱ፥ ሰው ረግጦኛልና ማረኝ፥ ሁልጊዜም ተዋጊ አስጨንቆኛል።


ሁልጊዜ ቃሎቼን ይጠመዝዙብኛል፥ በእኔ ላይም የሚመክሩት ሁሉ ለክፉ ነው።


እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።


የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተዋርደናልና።


በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥ የኃጥኣንንም ቅጣት ታያለህ።


እንደ ጐሽ አጠነከርከኝ፥ በአዲስ ዘይትም ቀባኸኝ።


እንዲህም ይሆናል፤ ሳይጠሩ እመልስላቸዋለሁ፥ ገናም ሲናገሩ እሰማለሁ።


እኔም አንተን ተከትዬ እረኛ ከመሆን አልቸኰልሁም፥ የመከራንም ቀን አልወደድሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣው በፊትህ ነበረ።


የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


በጌታ ቃል ይህን እንላችኋለን፤ እኛ ሕያዋን የሆንነው፥ ጌታም እስኪመጣ ድረስ የምንቀረው ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤


በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ፥ እርሱ ራሱ ያበረታችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ያቆማችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።


ሕያው ጌታ አለ፥ ጌታ ራሱ ይቀሥፈዋል፤ ወይም የመሞቻው ቀን ይመጣል፤ ወይም በጦርነት ይሞታል፤ ይጠፋልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች