Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 35:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እኔ ጌታ በእስራኤል ልጆች መካከል አድራለሁና የምትኖሩባትን በመካከልዋም የማድርባትን ምድር አታርክሱአት።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የምትኖሩባትን፣ እኔም የማድርባትን ምድር አታርክሷት እኔ እግዚአብሔር በእስራኤላውያን መካከል እኖራለሁና።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ስለ ሆንኩና በእናንተ በእስራኤል ሕዝብም መካከል ስለምኖር የእኔ መኖሪያ የሆነውንና እናንተ የምትኖሩበትን ምድር አታርክሱ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እና​ንተ በው​ስ​ጥዋ የም​ት​ኖ​ሩ​ባ​ትን፥ እኔም ከእ​ና​ንተ ጋር የማ​ድ​ር​ባ​ትን ምድር አታ​ር​ክ​ሱ​ኣት፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መካ​ከል የማ​ድር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እኔ እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆች መካከል አድራለሁና የምትኖሩባትን በመካከልዋም የማድርባትን ምድር አታርክሱአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 35:34
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በእስራኤል ልጆች መካከል አድራለሁ፤ ሕዝቤን እስራኤልንም ከቶ አልለያቸውም።”


“ይህች ለዘለዓለም ማረፊያዬ ናት፥ መርጫታለሁና በዚህች አድራለሁ።


በኢየሩሳሌም የሚያድር ጌታ ከጽዮን ይባረክ፥ ሃሌ ሉያ።


በመካከላቸው እንድኖር መቅደስ ይሥሩልኝ።


ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


“እነዚህ ሰዎች፤ ‘አድማ’ ብለው የሚጠሩትን፤ ማንኛውንም ነገር፤ ‘አድማ’ አትበሉ፤ እነርሱ የሚፈሩትን አትፍሩ፤ አትሸበሩለትም።


ምድሬንም በተጠሉ ጣዖቶቻቸው ሬሳዎች አርክሰዋልና፥ ርስቴንም አስጸያፊ በሆኑ ነገሮች ሞልተዋልና አስቀድሜ የበደላቸውንና የኃጢአታቸውን ዕዳ ሁለት እጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”


ጌታ በዚያ ሳለ፥ አንተ ግን፦ “እነዚህ ሁለቱ ሕዝቦችና እነዚህ ሁለቱ አገሮች ለእኔ ይሆናሉ እኛም እንወርሳቸዋለን” ብለሃልና፥


በጌታ ምድር ላይ አይቀመጡም፤ ኤፍሬምም ወደ ግብጽ ይመለሳል፥ በአሦርም ርኩስን ነገር ይበላሉ።


በሙሴና በአሮን ላይ ተሰብስበው እንዲህ አሉአቸው፦ “ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ ጌታም በመካከላቸው ነውና እናንተ እጅግ አብዝታችሁታል፤ በጌታም ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?”


ወንዱንና ሴቱን አውጡ፤ እኔ በመካከሉ የማድርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ ከሰፈሩ አወጡአቸው።”


በድኑን በዕንጨት ላይ እንደ ተሰቀለ አታሳድረው፤ ምክንያቱም በዕንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና፤ አምላክህ ጌታ ርስት አድርጎ የሚሰጥህን ምድር እንዳታረክስ በዚያኑ ዕለት ቅበረው።”


ጌታ ሆይ፤ ስለ ተቤዥኸው ሕዝብህ ስለ እስራኤል ብለህ ይህን ስርየት ተቀበል፤ ሕዝብህንም በፈሰሰው ንጹሕ ደም በደለኛ አታድርግ።’ ስለ ፈሰሰውም ደም ስርየት ይደረግላቸዋል።


በመካከልህ ያለው ጌታ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ነውና፥ የአምላክህ የጌታ ቁጣው እንዳይነድብህ፥ ከምድርም ፊት እንዳያጠፋህ።


ለበጉም በሆነው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት በቀር፥ ጸያፍ ነገር ሁሉ ርኩሰትና ውሸትም የሚያደርግ ሁሉ ወደ እርሷ ከቶ አይገባም።


ታላቅም ድምፅ ከሰማይ ከዙፋኑ ወጥቶ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች