Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 23:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ በሰባተኛው ወር፥ ወሩ በገባ በመጀመሪያው ቀን ፈጽሞ የምታርፉበት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ የምታውጁበት፥ የተቀደሰ ጉባኤ የምታደርጉበት ይሁንላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 “እስራኤላውያንን እንዲህ በላቸው፤ ‘የሰባተኛው ወር የመጀመሪያ ቀን ዕረፍት ይሁንላችሁ፤ በመለከት ድምፅም የሚከበር የተቀደሰ ጉባኤ ይኑራችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 “ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፤ በሰባተኛው ወር፥ ወሩ በገባ በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሔርን ለማምለክ በመለከት የታወጀ መታሰቢያ የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 “ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ በሰ​ባ​ተ​ኛው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ዕረ​ፍት፥ በመ​ለ​ከት ድምፅ መታ​ሰ​ቢያ፥ የተ​ቀ​ደ​ሰች ጉባኤ ትሁ​ን​ላ​ችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ዕረፍት፥ በመለከት ድምፅ መታሰቢያ፥ የተቀደሰ ጉባኤ ይሁንላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 23:24
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲሁ እስራኤል ሁሉ ሆ እያሉ፥ ቀንደ መለከትና እምቢልታ እየነፉ፥ ጸናጽልና መሰንቆም በገናም እየመቱ፥ የጌታን የቃል ኪዳን ታቦት አመጡ።


መለከቱንም የሚነፉ መዘምራኑም በአንድነት ሆነው በአንድ ድምፅ ጌታን እያመሰገኑና እያከበሩ፦ “ጌታ መልካም ነውና፥ ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና” ጌታን አመስግኑ እያሉ ድምጻቸውን ወደ ላይ ከፍ አድርገው በመለከትና በጸናጽል በዜማም ዕቃ ሁሉ ጌታን ባመሰገኑ ጊዜ፥ ደመናው ቤቱን፥ የጌታን ቤት ሞላው።


ከሰባተኛው ወር ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለጌታ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ጀመሩ፤ ነገር ግን የጌታ መቅደስ አልተመሠረተም ነበር።


ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን ወንዶች፥ ሴቶችና አስተውለው መስማት የሚችሉ ባሉበት በጉባኤው ሁሉ ፊት አመጣው።


የዙፋንህ መሠረት ጽድቅና ፍርድ፥ ምሕረትና እውነት በፊትህ ይሄዳሉ።


በዋሽንትና በመለከት ድምፅ በንጉሡ በጌታ ፊት እልል በሉ።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ከዚያም በኋላ በሰባተኛው ወር በአሥረኛው ቀን የቀንደ መለከትን ድምፅ ከፍ አድርገህ ታሰማለህ፤ በማስተስረያ ቀን በምድራችሁ ሁሉ የቀንደ መለከትን ድምፅ ታሰማላችሁ።


የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፥ ድንገት፥ በቅጽበተ ዐይን፥ መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።


ጌታ ራሱ በትእዛዝ ቃል በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፤ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች