Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 13:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 ይላጫል፥ ቈረቈሩ ግን አይላጭም፤ አሁንም ካህኑ ቈረቈር ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 ከቈሰለው ቦታ በቀር ጠጕሩን ይላጭ፤ ካህኑ ሰባት ተጨማሪ ቀን ሰውየውን ያግልል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 ያ ሰው ቊስሉን ሳይሆን በቊስሉ ዙሪያ ያለውን ጠጒር ይላጭ፤ ካህኑም እንደገና በሚያሳክከው በሽታ ምክንያት ለሰባት ቀን በቤት ውስጥ ተዘግቶበት እንዲቈይ ያድርግ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 ቈረ​ቈሩ ግን አይ​ላ​ጭም፤ ካህ​ኑም ቈር​ቈር ያለ​በ​ትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይለ​የ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 ቈረቈሩ ግን አይላጭም፤ ካህኑም ቈረቈር ያለበትን ሰው ሰባት ቀን ደግሞ ይዘጋበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 13:33
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካህኑ ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ከቆዳው በታች ዘልቆ ቢታይ፥ በውስጡም ቀጭን ብጫ ጠጉር ቢኖርበት፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ቈረቈር ነው፤ የራስ ወይም የአገጭ የለምጽ ደዌ ነው።


ካህኑም በሰባተኛው ቀን ደዌውን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ ባይሰፋ፥ በውስጡም ብጫ ጠጉር ባይኖር፥ የቈረቈሩም መልክ ከቆዳው በታች ባይዘልቅ፥


ካህኑም በሰባተኛው ቀን ቈረቈሩን ያያል፤ እነሆም፥ ቈረቈሩ በቆዳው ላይ ባይሰፋ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ ካህኑ፦ ንጹሕ ነው ይለዋል፤ ልብሱንም ያጥብና ንጹሕ ይሆናል።


ነገር ግን ቋቁቻው በሰውነቱ ቆዳ ላይ ቢነጣ፥ ከቆዳውም በታች ዘልቆ ባይታይ፥ በእርሱም ላይ ያለው ጠጉር ባይነጣ፥ ካህኑ የታመመውን ሰው ሰባት ቀን ይለየዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች