መሳፍንት 9:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 ወደ አቤሜልክም መልእክተኞች በምስጢር ልኮ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተው ከተማይቱ እንድትሸፍትብህ አድርገዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም31 ወደ አቢሜሌክም መልእክተኞች በምስጢር ልኮ እንዲህ አለ፤ “እነሆ፤ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተው ከተማዪቱ እንድትሸፍትብህ አድርገዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 በአሩማ ወዳለውም ወደ አቤሜሌክ መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት አሳሰባቸው፥ “የዔቤድ ልጅ ጋዓል ከወንድሞቹ ጋር ወደ ሴኬም መጥቶአል፤ በአንተም ላይ የከተማውን ሕዝብ አነሣሥቶአል። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 እንዲህም ብሎ ወደ አቤሜሌክ ከእጅ መንሻ ጋር መልእክተኞችን ላከ፥ “እነሆ፥ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሰቂማ መጥተዋል፤ እነሆም፥ በአንተ ምክንያት ከተማዪቱን ይወጓታል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 እንዲህም ብሎ ወደ አቤሜሌክ በተንኮል መልክተኞች ላከ፦ እነሆ፥ የአቤድ ልጅ ገዓልና ወንድሞቹ ወደ ሴኬም መጥተዋል፥ በአንተም ላይ ከተማይቱን አሸፍተዋል። ምዕራፉን ተመልከት |