መሳፍንት 7:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ጌዴዎንም የቀሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ አደረገ፤ ሦስት መቶውን ግን አስቀራቸው፤ እነርሱም የሚመለሱትን ሰዎች ስንቅና መለከት ወሰዱ። በዚህ ጊዜ የምድያማውያኑ ሰፈር ከእነርሱ በታች በሸለቆአማው ውስጥ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ጌዴዎንም የቀሩትን እስራኤላውያን በሙሉ ወደየድንኳናቸው እንዲመለሱ አደረገ፤ ሦስት መቶውን ግን አስቀራቸው፤ እነርሱም የሚመለሱትን ሰዎች ስንቅና መለከት ወሰዱ። በዚህ ጊዜ የምድያማውያኑ ሰፈር ከእነርሱ በታች በሸለቋማው ውስጥ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ስለዚህ ጌዴዎን የሕዝቡን ስንቅና እምቢልታዎቹን ከተረከቡት ከሦስት መቶዎቹ በቀር ሌሎቹን እስራኤላውያን ሁሉ ወደየቤታቸው እንዲመለሱ አሰናበታቸው፤ ይህም ሁሉ በሚሆንበት ጊዜ የምድያማውያን ሰፈር ከእነርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 የሕዝቡንም ስንቅና ቀንደ መለከት በእጃቸው ወሰዱ፤ የቀሩትንም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፤ ሦስቱን መቶ ሰዎች ግን በእርሱ ዘንድ ጠበቃቸው፤ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 የሕዝቡንም ስንቅና ቀንደ መለከት በእጃቸው ወሰዱ፥ የቀሩትንም የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ወደ ድንኳናቸው ሰደዳቸው፥ ሦስቱን መቶ ሰዎች ግን በእርሱ ዘንድ ጠበቃቸው፥ የምድያምም ሰፈር ከእርሱ በታች በሸለቆው ውስጥ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |