መሳፍንት 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍቺውን በሰማ ጊዜ ለጌታ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፥ “ጌታ የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ!” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ፍችውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፤ ከዚያም ወደ እስራኤላውያን ሰፈር ወጥቶ፣ “እግዚአብሔር የምድያማውያንን ሰፈር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷልና ተነሡ” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም15 ጌዴዎን ስለ ሰውየው ሕልምና ስለ ፍቹም ምንነት በሰማ ጊዜ በጒልበቱ ተንበርክኮ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤላውያንም ሰፈር ተመልሶ “እግዚአብሔር በምድያማውያንና በሠራዊቱ ላይ ድልን የሚያቀዳጃችሁ ስለ ሆነ ተነሡ!” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜዉን በሰማ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፥ “እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)15 ጌዴዎንም ሕልሙንና ትርጓሜውን በሰማ ጊዜ ሰገደ፥ ወደ እስራኤልም ሰፈር ተመልሶ፦ እግዚአብሔር የምድያምን ሠራዊት በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአልና ተነሡ አለ። ምዕራፉን ተመልከት |