መሳፍንት 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የጌታን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የጌታ ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 የዝማሬ ድምፅ ስሙ። ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል። “ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እነሆ አድምጡ! ውሃ በሚቀዳባቸው ጒድጓዶች ዙሪያ የሚሰማው የብዙ ሰዎች ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ድል ያበሥራል፤ የእስራኤልንም ሕዝብ ድል አድራጊነት ይናገራል። ከዚህ በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ፥ ከከተሞቻቸው ተሰልፈው ወረዱ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 በብዙዎች ደስተኞች መካከል መሰንቆን ምቱ፤ በዚያ ለእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራን፥ በእስራኤልም ውስጥ ጽድቅንና ኀይልን ያቀርባሉ። ያንጊዜም የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ ከተማዎቹ ወረዱ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 በማጠጫው መካከል ካሉት ከቀስተኞች ጩኸት ርቀው፥ በዚያ የእግዚአብሔርን ጽድቅ፥ በእስራኤል ላይ የግዛቱን ጽድቅ ይጫወታሉ፥ ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ሕዝብ ወደ በሮች ወረዱ። ምዕራፉን ተመልከት |