Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መሳፍንት 4:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ባራቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፥ ያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከእርሷ ጋር ወደ ድንኳንዋ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ባርቅ ሲሣራን በመከታተል ላይ ስለ ነበር ከዚያ ሲደርስ፣ ኢያዔል ከድንኳኗ ወጥታ “ና፤ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው፤ ስለዚህ ከርሷ ጋራ ወደ ድንኳኗ ገባ፤ ሲሣራም በጆሮ ግንዱ ላይ ካስማ እንደ ተመታበት ሞቶ ተዘርሮ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ባራቅ ሲሣራን እያሳደደ ሲመጣ ያዔል ልትቀበለው ወጥታ “ወደዚህ ና! አንተ የምትፈልገውን ሰው አሳይሃለሁ” አለችው። ስለዚህም ከእርስዋ ጋር ወደ ውስጥ በገባ ጊዜ የድንኳኑ ካስማ በሲሣራ ጆሮ ግንድ ላይ እንደ ተቸነከረ ሬሳውን በመሬት ላይ ተጋድሞ አየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 እነ​ሆም፥ ባርቅ ሲሣ​ራን ሲያ​ባ​ርር ኢያ​ዔል ልት​ገ​ና​ኘው ወጥታ፥ “ና፤ የም​ት​ሻ​ውን ሰው አሳ​ይ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ እነ​ሆም፥ ሲሣ​ራን ወድቆ፥ ሞቶም አገ​ኘው፤ ካስ​ማ​ውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 እነሆም፥ ባርቅ ሲሣራን ሲያባርር ኢያዔል ልትገናኘው ወጥታ፦ ና የምትሻውንም ሰው አሳይሃለሁ አለችው። ወደ እርስዋም ገባ፥ እነሆም፥ ሲሣራን ወድቆ ሞቶም አገኘው፥ ካስማውም ከጆሮግንዱ ውስጥ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መሳፍንት 4:22
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡን ሁሉ ወደ አንተ እመልሳለሁ፤ አንተ የምትፈልገው የአንድ ሰው መሞት ብቻ ነውና፥ ሕዝቡ ሁሉ በሰላም ይኖራል።”


የሔቤር ሚስት ያዔል ግን ሲሣራ ደክሞ፥ ከባድ እንቅልፍም ወስዶት ሳለ፥ የድንኳን ካስማና መዶሻ ይዛ በቀስታ ወደ እርሱ ቀረበች፤ ከዚያም ካስማውን በመዶሻ ጆሮ ግንዱ ላይ መትታ ከመሬት ጋር ሰፋችው፤ እርሱም ሞተ።


በዚያች ዕለት እግዚአብሐር የከነዓንን ንጉሥ ኢያቢስን በእስራኤላውያን ፊት እንዲሸነፍ አደረገው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች