Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መሳፍንት 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሲሣራም፥ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ጮጮውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደገናም ሸፈነችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሲሣራም፣ “ጠምቶኛልና እባክሽን ውሃ አጠጪኝ” አላት፤ እርሷም የወተት ዕቃውን ከፍታ የሚጠጣውን ሰጠችው፤ እንደ ገናም ሸፈነችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ሲሣራም “እባክሽ የምጠጣው ውሃ ስጪኝ፤ በጣም ጠምቶኛል” አላት፤ እርስዋም ከቈዳ የተሠራውን የወተት ዕቃ ከፍታ አጠጣችውና እንደገና ሸፍና ደበቀችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ሲሣ​ራም፥ “ጠም​ቶ​ኛ​ልና እባ​ክሽ የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እር​ስ​ዋም የወ​ተ​ቱን ዕቃ ፈትታ አጠ​ጣ​ችው፤ ፊቱ​ንም ሸፈ​ነ​ችው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እርሱም፦ ጠምቶኛልና እባክሽ የምጠጣው ጥቂት ውኃ ስጭኝ አላት፥ እርስዋም የወተቱን አቁማዳ ፈትታ አጠጣችው፥ ሸፈነችውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መሳፍንት 4:19
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ እኔ በውኃው ምንጭ ላይ ቆሜአለሁ፥’ ውኃ ልትቀዳ ለምትመጣውም ቆንጆ፦ ‘ጥቂት ውኃ ከእንስራሽ አጠጪኝ’ ስላት፥


ስለዚህ ኤልያስ ወደ ሰራጵታ ሄደ፤ ወደ ከተማይቱም ቅጽር በር በደረሰ ጊዜ አንዲት ባሏ የሞተባት ሴት እንጨት ስትለቅም አይቶ “እባክሽ የምጠጣው ውሃ አምጪልኝ” አላት።


ድሆችና ምስኪኖችም ውኃ ይሻሉ አያገኙምም፥ ምላሳቸውም በጥማት ደርቋል፤ እኔ ጌታ እሰማቸዋለሁ፥ የእስራኤል አምላክ እኔ አልተዋቸውም።


አንዲት የሰማርያ ሴት ውሃ ልትቀዳ መጣች። ኢየሱስም “ውሃ አጠጪኝ” አላት፤


ያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበ ለችውና፥ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው።


እርሱም፥ “በድንኳኑ በር ላይ ቁሚ፤ ማንም ሰው መጥቶ፥ ‘እዚህ ሰው አለ?’ ቢልሽ፥ ‘የለም በይ’” አላት።


የቄናዊው የሔቤር ሚስት ያዔል ከሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን፥ በድንኳን ውስጥ ከሚኖሩ ሴቶች ይልቅ የተባረከች ትሁን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች