መሳፍንት 18:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 በዚያን ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ የዳን ነገድም በእስራኤል ነገዶች መካከል የርስት ድርሻውን ገና ስላልወሰደ፥ የሚሰፍርበትን የራሱን ርስት ይፈልግ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 በዚያ ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም። የዳን ነገድም በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስተ ድርሻውን ገና ስላልወሰደ፣ የሚሰፍርበትን የራሱን ርስት ይፈልግ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 በዚያም ዘመን በእስራኤል ንጉሥ አልነበረም፤ በእስራኤል ነገዶች መካከል የራሳቸው የሆነ የርስት ድርሻ ገና ያላገኙ ስለ ነበሩ የዳን ነገድ ተወላጆች የሚሰፍሩበትን ርስት ለማግኘት በመፈለግ ላይ ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም። እስከዚያም ቀን ድረስ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበርና በዚያ ዘመን የዳን ነገድ የሚቀመጡባት ርስት ይሹ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 በዚያም ዘመን በእስራኤል ዘንድ ንጉሥ አልነበረም። እስከዚያም ቀን ድረስ ለዳን ነገድ በእስራኤል ነገዶች መካከል ርስት አልደረሳቸውም ነበርና በዚያ ዘመን የሚቀመጡባት ርስት ይሹ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |