መሳፍንት 15:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ሳምሶንም፥ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፥ ሺህ ሬሳ አነባባሪ!” ብሎ ፎከረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ሳምሶንም፣ “በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሰው ዘራሪ፤ በአንድ የአህያ መንጋጋ፣ ሺሕ ሬሳ አነባባሪ” ብሎ ፎከረ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ሶምሶንም፥ “በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገደልኩ፤ በዚህም የአህያ መንጋጋ ሬሳውን በሬሳ ላይ ከመርሁ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ሶምሶንም፥ “በአህያ መንጋጋ አጥንት ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፤ በአህያ መንጋጋ አጥንት አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁና” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ሶምሶንም፦ በአህያ መንጋጋ ክምር በክምር ላይ አድርጌአቸዋለሁ፥ በአህያ መንጋጋ አንድ ሺህ ሰው ገድያለሁ አለ። ምዕራፉን ተመልከት |