Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መሳፍንት 14:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋር እንደተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋራ እንደ ተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ከማሩም ጥቂት በእጁ ቈርጦ እየበላ መንገዱን ቀጠለ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱ ቀርቦ ከያዘው ማር. ሰጥቶአቸው በሉ፤ ነገር ግን ሶምሶን ያንን ማር. ያገኘው ከሞተው አንበሳ በድን ውስጥ መሆኑን አልነገራቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ወስ​ዶም በላ፤ እየ​በ​ላም ሄደ፤ ወደ አባ​ቱና ወደ እና​ቱም ደረሰ፤ ሰጣ​ቸ​ውም፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ማሩ​ንም ከአ​ን​በ​ሳው አፍ ውስጥ እን​ዳ​ወ​ጣው አል​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 በእጁም ወስዶ መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፥ ወደ አባቱና ወደ እናቱ መጣ፥ ማሩንም ሰጣቸው፥ እነርሱም በሉ፥ ማሩንም ከአንበሳው ሬሳ ውስጥ እንደ ወሰደ አልነገራቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መሳፍንት 14:9
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልጄ ሆይ፥ መልካም ነውና ማር ብላ፥ ወለላም ለጣምህ ጣፋጭ ነው።


በትዕግሥት አለቃ ይለዝባል፥ ገር ምላስ አጥንትን ይሰብራል።


የሳምሶን አባት ልጅቱን ሊያይ ወረደ፤ ሳምሶንም በወጣቶች የተለመደ በነበረው መሠረት በዚያ ግብዣ አደረገ።


ከጥቂት ቀን በኋላም ሊያገባት ተመለሰ፤ የአንበሳውንም በድን ለማየት ከመንገድ ዘወር አለ፤ በበድኑም ውስጥ የንብ መንጋ ሰፍሮ ተመለከተ፤ ማርም ነበረበት፤


ሳኦልም መልሶ፥ “አህዮቹ መገኘታቸውን ገልጦ ነገረን” አለው። ነገር ግን ስለ መንገሡ ሳሙኤል የነገረውን ለአጎቱ አልተናገረም።


አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፥ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች