Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መሳፍንት 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናንቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ በዚያም ከአንድ የወይን አትክልት ቦታ እንደ ደረሱ፥ ድንገት አንድ የአንበሳ ደቦል እያገሣ መጣበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ከዚያም ሳምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋራ ወደ ተምና ወረደ፤ በዚያም ከአንድ የወይን አትክልት ቦታ እንደ ደረሱ፣ ድንገት አንድ የአንበሳ ደቦል እያገሣ መጣበት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ከዚህ በኋላ ሶምሶን ከአባቱና ከእናቱ ጋር ወደ ቲምና ወረደ፤ እዚያም በወይን ተክል ውስጥ አልፈው ሲሄዱ አንድ ደቦል አንበሳ እያገሣ መጣበት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሶም​ሶ​ንም፥ አባ​ቱና እና​ቱም ወደ ቴም​ናታ ወረዱ፤ በቴ​ም​ና​ታም ወዳ​ለው ወደ ወይኑ ስፍራ ፈቀቅ አለ፤ እነ​ሆም፥ የአ​ን​በሳ ደቦል እያ​ገሣ መጣ​በት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሶምሶንም አባቱና እናቱም ወደ ተምና ወረዱ፥ በተምናም ወዳለው ወደ ወይኑ ስፍራ መጡ፥ እነሆም፥ የአንበሳ ደቦል እያገሣ ወደ እርሱ ደረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መሳፍንት 14:5
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የቃብጽኤል አገር ሰው የሆነው የዮዳሄ ልጅ በናያም ታላቅ ተግባር የፈፀመ ሌላው ጐበዝ ተዋጊ ነበረ፤ ሁለቱን በጣም የታወቁ የሞዓብን ሰዎችን ገድሎአል፤ እንዲሁም በረዶ በጣለበት ዕለት በጉድጓድ ውስጥ ገብቶ አንበሳ ገድሎአል፤


በቀብስኤልም የነበረው፥ ታላቅ ሥራ ያደረገው የጽኑዕ ሰው የዮዳሄ ልጅ በናያስ የሞዓባዊን የአሪኤልን ሁለቱን ልጆች ገደለ፤ በአመዳይም ወራት ወርዶ በጉድጓድ ውስጥ አንበሳ ገደለ።


በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።


የአንበሳ ደቦሎች በእርሱ ላይ አገሡ፥ ድምፃቸውንም አሰሙ፤ ምድሩንም ባድማ አደረጉ፥ ከተሞቹም ፈርሰዋል የሚቀመጥባቸውም የለም።


እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤


ድንበሩም ከበኣላ በምዕራብ በኩል ወደ ሴይር ተራራ ዞረ፤ ክሳሎን ወደምትባል ወደ ይዓርም ተራራ ወገን በሰሜን በኩል አለፈ፤ ወደ ቤት ሳሚስ ወረደ፥ በተምና በኩልም አለፈ።


በመጠን ኑሩ፤ ንቁም! ጠላታችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን በመፈለግ እንደሚያገሣ አንበሳ ዙሪያውን ይንጐራደዳል።


በዚያን ጊዜ በእስራኤል ላይ ገዦቹ ፍልስጥኤማውያን ስለ ነበሩ፥ ከፍልስጥአማውያን ጋር ጠብ እንዲፈጠር ጌታ ሆን ብሎ ያደረገው ነገር መሆኑን አባቱና እናቱ አላወቁም ነበር።


በዚህ ጊዜ የጌታ መንፈስ በኃይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደርገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር።


ተከትዬ በመሄድ እመታውና ከአፉ አስጥል ነበር፤ ፊቱን ወደ እኔ በሚያዞርበትም ጊዜ ጉሮሮውን ይዤ በመምታት እገድለው ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች