Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መሳፍንት 14:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፥ “ለካስ ትጠላኛለህ በእርግጥ አትወደኝም” አለችው። እርሱም፥ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ከዚያ የሳምሶን ሚስት ተንሰቅስቃ እያለቀሰች ከፊቱ በመቅረብ፣ “ለካስ ትጠላኛለህ! በርግጥ አትወድደኝም” አለችው። እርሱም፣ “ይህን ለአባቴም ሆነ ለእናቴ አልነገርኋቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ ለምን እነግርሻለሁ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ስለዚህ የሶምሶን ሚስት እያለቀሰች ወደ እርሱ ቀርባ “ለካስ አንተ እኔን አትወደኝም! እንዲያውም በጣም ትጠላኛለህ! የአገሬን ልጆች እንቆቅልሽ ጠይቀህ ለእኔ እስከ አሁን ፍቺውን አልነገርከኝም!” አለችው። እርሱም “እነሆ! እኔ ይህን ለአባቴና ለእናቴ እንኳ አልነገርኳቸውም፤ ታዲያ ለአንቺ የምነግርበት ምክንያት ምንድን ነው?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የሶ​ም​ሶ​ንም ሚስት በፊቱ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ች​በት፥ “ጠል​ተ​ኸ​ኛል፤ ከቶም አት​ወ​ድ​ደ​ኝም፤ ለሕ​ዝቤ ልጆች የነ​ገ​ር​ኸ​ውን እን​ቆ​ቅ​ል​ሽ​ህን አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝ​ምና” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “እነሆ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ናቴ አል​ነ​ገ​ር​ኋ​ቸ​ውም፤ ለአ​ንቺ እነ​ግ​ር​ሻ​ለ​ሁን?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 የሶምሶንም ሚስት በፊቱ እያለቀሰች፦ በእውነት ጠልተኸኛል፥ ከቶም አትወድደኝም፥ ለሕዝቤ ልጆች እንቈቅልሽ ሰጥተሃቸዋልና ትርጓሜውንም አልነገርኸኝም አለችው። እርሱም፦ እነሆ፥ ለአባቴና ለእናቴ አልነገርኋቸውም፥ ለአንቺ እነግርሻለሁን? አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መሳፍንት 14:16
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ ሰው አባቱንና እናቱን ትቶ ከሚስቱ ጋር ይተባበራል፤ ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ።


ሚስቱም በሰርጉ በዓል ሰባት ቀን ሙሉ እያለቀሰች ጨቀጨቀችው፤ አጥብቃ ስለ ነዘነዘችውም በመጨረሻ በሰባተኛው ቀን ነገራት፤ እርሷም በበኩሏ የእንቈቅልሹን ፍች ለሕዝቧ ነገረች።


ከዚያም፥ “ሳታምነኝ እንዴት ‘እወድሻለሁ’ ትለኛለህ? ስታታልለኝና የኃይልህንም ታላቅነት ምስጢር ስትደብቀኝ ይህ ሦስተኛ ጊዜህ ነው” አለችው።


በሕይወት መኖሩን እስኪጠላ ድረስ ዕለት ዕለት በመጨቅጨቅ አሰለቸችው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች