መሳፍንት 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተላት፤ ሰውየው እንደደረሰም፥ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርኸው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፤ “አዎን እኔ ነኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተላት፤ ሰውየው እንደ ደረሰም፣ “ከሚስቴ ጋራ ተነጋግረህ የነበርኸው አንተ ነህ?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፤ “አዎን እኔ ነኝ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ማኑሄም ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሚስቱን ተከትሎ ሄደ፤ ወደ ሰውየውም ቀርቦ “ከሚስቴ ጋር ተነጋግረህ የነበርከው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። ሰውየውም “አዎ! እኔ ነኝ” ሲል መለሰ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተለ፤ ወደ ሰውዬዉም መጥቶ፥ “ከሚስቴ ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን?” አለው። መልአኩም፥ “እኔ ነኝ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ማኑሄም ተነሥቶ ሚስቱን ተከተለ፥ ወደ ሰውዮውም መጥቶ፦ ከዚህች ሴት ጋር የተነጋገርህ አንተ ነህን? አለው። እርሱም፦ እኔ ነኝ አለ። ምዕራፉን ተመልከት |