ኢያሱ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሱ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በጌታ ታቦት ፊት ይሸከሙ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ የነዌ ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፣ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባት ካህናትም ሰባት ቀንደ መለከት ይዘው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ኢያሱም ካህናቱን ጠርቶ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ከእናንተም ሰባታችሁ እምቢልታ ይዛችሁ ከታቦቱ ፊት ቅደሙ።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፤ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላቸው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸከሙ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት ወስደው በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አላቸው። ምዕራፉን ተመልከት |