Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 8:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የሚጠሉህ ኃፍረት ይከናነባሉ፥ የክፉዎችም ድንኳን አይገኝም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ጠላቶችህ ኀፍረት ይለብሳሉ፤ የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የሚጠሉህ ሰዎች ግን የኀፍረት ሸማ ይከናነባሉ፤ የክፉ ሰዎችም ቤቶች ይጠፋሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ኀፍ​ረ​ትን ይለ​ብ​ሳሉ፤ የኀ​ጢ​ኣ​ተ​ኞ​ችም ቤት ይጠ​ፋል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የሚጠሉህ እፍረት ይለብሳሉ፥ የኃጢአተኞችም ድንኳን አይገኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 8:22
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የአምላክ አልባ ሰው ጉባኤ ፍሬ የለውም፥ የጉቦ ድንኳኖችንም እሳት ትበላለች።


ከሚታመንበት ድንኳን ይነቀላል፥ ወደ ድንጋጤም ንጉሥ ያስቸኩሉታል።


እናንተ፦ የከበርቴው ቤት የት ነው? ክፉዎች ያደሩበት ድንኳን የት ነው? ብላችኋል።


እርሱ በደለኛን በሕይወት አይጠብቅም፥ ለችግረኞች ግን ይፈርዳል።


ገመዳቸው የተነቀለ አይደለምን? አለጥበብም ይሞታሉ።’”


ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”


ቤቱን ይደገፈዋል፥ ነገር ግን አይቆምለትም፥ ይይዘውማል፥ አይጸናለትም።


ከቦታው ቢጠፋ፦ አላየሁህም ብሎ ይክደዋል።


ኢዮብም መለሰ፤ እንዲህም አለ፦


የሚከሱኝ እፍረትን ይልበሱ፥ እፍረታቸውን እንደ መጐናጸፊያ ይልበሱአት።


ጠላቶቹንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፥ በእርሱ ግን ዘውዱ ያንጸባርቃል።”


በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቁሉ፥ በእኔ ላይ የሚታበዩ እፍረትንና ጉስቁልናን ይልበሱ።


የኀጥኣን ቤት ይፈርሳል፥ የቅኖች ማደሪያ ግን ያብባል።


በዚያን ጊዜ የባሕር አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ያስቀምጣሉ፥ ወርቀዘቦ ልብሳቸውንም ያወልቃሉ፤ መንቀጥቀጥን ይለብሳሉ፥ በመሬት ላይ ይቀመጣሉ፥ ሁልጊዜም ይንቀጠቀጣሉ፥ በአንቺም ይደነቃሉ።


ንጉሡ ያለቅሳል፥ ልዑሉም ውርደትን ይለብሳል፥ የምድሪቱም ሕዝቦች እጆች ይንቀጠቀጣሉ፥ እንደ መንገዳቸው መጠን አደርግባቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም መጠን እፈርድባቸዋለሁ፥ በዚያን ጊዜ እኔ ጌታ እንደሆንሁ ያውቃሉ።


እኔ እልከዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ወደሚሰርቀውም ቤት፥ በሐሰትም በስሜ ወደሚምለው ቤት ይገባል፤ በቤታቸውም ውስጥ ይኖራል፥ እንጨቱንና ድንጋዩን፥ ይበላል።”


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች