Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ከዚህ ሥጋ ይልቅ ነፍሴ መታነቅንና ሞትን መረጠች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህ እንዲህ ሆኖ ከመኖር፣ መታነቅና መሞትን እመርጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ይህን ሥቃይ የበዛበት ሰውነት ተሸክሜ ከመኖር ታንቄ መሞትን እመርጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ሕይ​ወ​ትን ከመ​ን​ፈሴ ትለ​ያ​ለህ። አጥ​ን​ቶ​ቼ​ንም ከሞት ትጠ​ብ​ቃ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ነፍሴም ከአጥንቴ ይልቅ መታነቅንና ሞትን መረጠች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 7:15
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አኪጦፌልም ምክሩን እንዳልተከተሉት ባየ ጊዜ፥ አህያውን ጭኖ ቤቱ ወደሚገኝበት ወደ መኖሪያ ከተማው ሄደ፤ ቤቱንም አስተካክሎ በገዛ እጁ ታነቀ፤ ከሞተ በኋላ በአባቱም መቃብር ተቀበረ።


የተሰወረ ሀብትን ከሚቈፍሩ ይልቅ ሞትን ለሚጠብቁ ለማያገኙትም፥


መቃብርን ባገኙ ጊዜ በእልልታ ደስ ለሚላቸው፥ ሐሤትንም ለሚያደርጉ ሕይወት ስለምን ተሰጠ?


አንተ በሕልም ታስፈራራኛለህ፥ በራእይም ታስደነግጠኛለህ፥


ሕይወቴን ናቅኋት፥ ለዘለዓለም ልኖር አልወድድም፥ ቀኖቼ እስትንፋስ ናቸውና ተወኝ።


ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፥ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።


ከፀሐይም በታች የተሠራው ሥራ ሁሉ ከብዶብኛልና ሕይወትን ጠላሁ፥ ሁሉም ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።


እኔም ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚህም ክፉ ወገን የቀሩትን ትሩፋን ሁሉ፥ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


አሁንም፥ ጌታ ሆይ፥ ከሕይወት ሞት ይሻላልና፥ እባክህ ነፍሴን ከእኔ ውሰድ።”


ፀሐይም በወጣ ጊዜ እግዚአብሔር የሚያቃጥል የምሥራቅ ነፋስ አዘጋጀ፥ ዮናስ ራሱን እስኪስት ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለነፍሱም ሞትን ለመነና “ከሕይወት ሞት ይሻላል” አለ።


ብሩን በቤተ መቅደስ ጥሎ ወጣ፤ ሄዶም ታንቆ ሞተ።


በዚያም ቀኖች ሰዎች ሞትን ይፈልጋሉ፤ አያገኙትምም፤ ሊሞቱም ይመኛሉ፤ ሞትም ከእነርሱ ይሸሻል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች