Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 5:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ድንኳንህ ሰላምን እንደሚያገኝም ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ፥ አንዳችም አይጐድልብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ድንኳንህ በሚያስተማምን ሁኔታ እንዳለ ታውቃለህ፤ በረትህን ትቃኛለህ፤ አንዳችም አይጐድልብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 በድንኳንህ ሰላም እንደሚሰፍን ታረጋግጣለህ፤ የበጎችህንም በረት ስትጐበኝ ሁሉን በደኅና ታገኛቸዋለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ያን​ጊዜ ቤትህ በሰ​ላም እን​ዲ​ሆን ታው​ቃ​ለህ፤ ከን​ብ​ረ​ት​ህም አን​ዳች አይ​ጐ​ድ​ልም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ድንኳንህም በሰላም እንዲሆን ታውቃለህ፥ በረትህን ትጐበኛለህ አንዳችም አይጐድልብህም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 5:24
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በድንኳኑ ውስጥ ለእርሱ የማይሆነው ይኖራል፥ በመኖሪያውም ላይ ዲን ይበተናል።


በእውነት የኃጢአተኞች ቤት እንዲሁ ናት፥ እግዚአብሔርንም የማያውቅ ሰው ስፍራ ይህ ነው።”


ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥ መብራቱም በላዩ ይጠፋል።


ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል።


በበረሃ፥ በምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፥ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም።


በመኰንኖችም ላይ ውርደትን ዘረገፈ፥ መንገድም በሌለበት በምድረ በዳ አንከራተታቸው።


ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።


ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።


ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።


ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤


“ስትገባ ትባረካለህ፤ ስትወጣም ትባረካለህ።


ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ጺቅላግ እንደ ደረሱም፥ እነሆ፤ ከተማዪቱ በእሳት ጋይታ፥ ሚስቶቻቸው፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸው ተማርከው አገኙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች