ኢዮብ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ያን ሌሊት ጨለማ ይያዘው፥ በዓመቱ ቀኖች መካከል ደስ አይበለው፤ በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቈጠር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ ከዓመቱ ቀናት ጋራ አይቈጠር፤ ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ያን ሌሊት ድቅድቅ ጨለማ ይሸፍነው፤ ከዓመቱ ቀኖች ጋር አይቈጠር፤ ከወሮቹም ውስጥ ገብቶ አይታሰብ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ያች ቀንም የተረገመች ትሁን። ያችም ሌሊት ጨለማ ይምጣባት፤ በዓመቱ ቀኖች መካከል አትኑር፤ በወሮች ቀኖች ውስጥም ገብታ አትቈጠር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ያን ሌሊት ጨለማ ይያዘው፥ በዓመቱ ቀኖች መካከል ደስ አይበለው፥ በወሮች ውስጥ ገብቶ አይቈጠር። ምዕራፉን ተመልከት |