Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 24:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 የወላጅ አልባውን አህያ ይነዳሉ፥ የመበለቲቱን በሬ ለመያዣነት ይወስዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 የድኻ አደጉን አህያ ቀምተው ይሄዳሉ፤ የመበለቲቱንም በሬ በመያዣነት ይወስዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 የድኻ አደጉን አህያ ይቀማሉ፤ ባልዋ የሞተባትን ሴት ንብረት የሆነውንም በሬ፥ በመያዣ ስም ይወስዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 የድ​ሃ​አ​ደ​ጎ​ቹን አህያ ይነ​ዳሉ የመ​በ​ለ​ቲ​ቱ​ንም በሬ ስለ መያዣ ይወ​ስ​ዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 የድሀ አድጎቹን አህያ ይነዳሉ፥ የመበለቲቱን በሬ ስለ መያዣ ይወስዳሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 24:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በድሀ አደጉ ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ፥ ለወዳጆቻችሁም ጉድጓድ ትቈፍራላችሁ።


የሚለብሰው ሌላ የለውም፥ ገላውን የሚሸፍንበት እርሱ ብቻ ነውና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ መሐሪ ነኝና እሰማዋለሁ።


“ወፍጮና መጁን ወይም መጁንም ቢሆን፥ የብድር መያዣ አድርገህ አትውሰድ፤ የሰውን ነፍስ መያዣ አድርጎ መውሰድ ይሆናልና።


“አንድ ሰው ከእስራኤላውያን ወንድሞቹ አንዱን ፈንግሎ በመውሰድ ባርያ ሲያደርገው ወይም ሲሸጠው ቢገኝ፥ ፈንጋዩ ይሙት። በዚህ ዓይነት ክፉውን ነገር ከመካከልህ ታስወግዳለህ።


እነሆ፤ ከፊታችሁ ቆሜአለሁ፤ በእግዚአብሔርና እርሱ በቀባው ፊት መስክሩብኝ፤ የማንን በሬ ወሰድሁ? የማንን አህያ ወሰድሁ? ማንን አታለልሁ? በማንስ ላይ ግፍ ሠራሁ? አይቶ እንዳላየ ለመሆንስ ከማን እጅ ጉቦ ተቀበልሁ? ከእነዚህ ሁሉ አንዱን እንኳ አድርጌ ከሆነ እመልስላችኋለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች