Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢዮብ 22:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በዚያ ጊዜ በሁሉን ቻይ አምላክ ደስ ይልሃል፤ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታቀናለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፤ በእርሱም ተማምነህ ትኖራለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሞገ​ስን ታገ​ኛ​ለህ። ወደ ሰማ​ይም በደ​ስታ ትመ​ለ​ከ​ታ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 የዚያን ጊዜ ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይልሃል፥ ፊትህንም ወደ እግዚአብሔር ታነሣለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢዮብ 22:26
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ጊዜ በእውነት ፊትህን ያለ ነውር ታነሣለህ፥ ትበረታለህ፥ አትፈራምም።


ሕይወትህ ከቀትር ይልቅ ያበራል፥ ጨለማም ቢሆን እንደ ጥዋት ይሆናል።


ሁሉን የሚችል አምላክ ወርቅና የሚብለጨለጭ ብር ይሆንልሃል።


ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?


ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ይሰማዋል፥ ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፥ ለሰውም የጽድቁን ዋጋ ይመልስለታል።


ትእዛዞችህንም ሁሉ ስመለከት በዚያን ጊዜ አላፍርምና።


አንተን ታምኛለሁና በማለዳ ጽኑ ፍቅርህን አሰማኝ፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አንሥቻለሁና የምሄድበትን መንገድ አሳውቀኝ።


የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።


በጌታ ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።


የአገልጋይህን ነፍስ ደስ አሰኛት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን ወደ አንተ አነሣለሁና።


በዱር እንዳለ እንኮይ፥ እንዲሁ ውዴ በጐልማሶች መካከል ነው። ከጥላው በታች እጅግ ወድጄ ተቀመጥሁ፥ ፍሬውም ለጉሮሮዬ ጣፋጭ ነው።


በዚያን ጊዜ በጌታ ደስ ይልሃል፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ አወጣሃለሁ፥ የአባትህንም የያዕቆብን ርስት አበላሃለሁ፤ ይህን የጌታ አፍ ተናግሮአልና።


በውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥


ትእዛዛቱን ስለምንጠብቅ፥ በፊቱም ደስ የሚያሰኘውን ስለምናደርግ፥ የምንለምነውን ሁሉ ከእርሱ እናገኛለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች